ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃ ባለቤት ለመሆን የመረጃ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ
ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃ ባለቤት ለመሆን የመረጃ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ
ባለፉት ዓመታት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ጉልህ ስኬቶች መመዝገባቸውን ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖን - ETEX- 2025 የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ባድረጉት የመክፈቻ ንግግር ባለፉት ዓመታት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ገልጸዉ ይህም ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን አቅም ለመገንባት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም ጠቁመዋል።
ተለዋዋጩን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት ሁለንተናዊ ደህንነትንና የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃ እና ዲጂታል ዳታ ባለቤት ለመሆን የመረጃ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሥራዎችን እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝዳንቱ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃ እና ዲጂታል ዳታ ባለቤት ለመሆን የመረጃ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፣ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሥራዎችን እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የመረጃ ደህንነትን ለመጠበቅ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎትን ለማቅረብ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነም አክለው ተናግረዋል፡፡
ትውልዱ ከዘመኑ ጋር አንዲራመድ ዲጂታል ፋይናንሲንግ ወሳኝ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ይህን አፍሪካን ከዓለም ጋር የሚያስተሳስረውን ሥራ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ይህንን እውን ለማድረግም የሳይበር ደህንነት መሰረታዊ ነገር መሆኑን በመጥቀስ፣ በዚህ ረገድ ከኤክስፖው ትልቅ ተሞክሮ ይገኛል ብለዋል።
ኤክስፖዉ ከዛሬ ከግንቦት 8-10/2017 ይቆያል።