የጥንቃቄ መልዕክት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ከፍተኛ የሚባል የይለፍ ቃል ጥቃቶች እየተከስቱ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሚስጥራዊ መረጃዎች መሹለካቸዉን ተከትሎ ከ184 ሚሊዮን በላይ የይለፍ-ቃሎች ለጥቃት መጋለጣቸዉ በዘርፉ የተካሄደ ጥናት አመልክቷል።

በተለያዩ የሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገው ይኸው ጥናት እንደ ZDnet፣ Techradar ፣ PCMage እንዲሁም Forbes በመሳሰሉ ድረ-ገጾች የወጣዉ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ 1.8 ቢሊዮን መዝገቦች መሹለካቸዉን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑት እንደ ጎግል፣ ማይክሮሶፍት፣ አፕል፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም ከመሳሰሉት ፕላትፎርሞች ጋር የተያያዙ ከ184 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የይለፍ ቃሎች ሾልከዉ በመዉጣታቸዉ ተጠቃሚዎች ለጥቃት መጋለጣቸው ተጠቁሟል።

የመረጃ ጥቃት መድረሱን መነሻ በማድረግ በተላለፈው መልዕክት 1.8 ቢሊዮን መዝገቦች መሽሎካቸው በመታወቁ ተጠቃሚዎች ሊከስቱ ከሚችሉ ጥቃቶች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

በተጠቀሱት ፕላትፎርሞች ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚጠቀሟቸዉን የይለፍ ቃሎች በመቀየር ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም እንደሚኖርባቸው ያነሳው ጥናቱ ለተለያዩ አካዉንቶች ተመሳሳይ የይለፍ- ቃል መጠቀም ተገቢ እንዳልሆነ መክሯል።

የይለፍ- ቃሎችን ከመቀየራችን ባሻገር ባለ ሁለት ደረጃ የደኅንነት ማረጋገጫ (2FA) ከመጠቀም ባለፈ አጠራጣሪ ሊንኮችን ወይም ኢ-ሜይሎችን ከመክፈት መቆጠብ እንደሚገባም አሳስቧል።