በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ የሚልቀውን በማክሸፍ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን ተችሏል

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

በኢትዮጵያ 11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች 97 በመቶ የሚልቀውን በማክሸፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ገለጸ።

የሳይበር ጥቃቱ በፋይናንስ እና የሚዲያ ተቋማት ላይ በብዛት ኢላማ ያደረገ መሆኑም ታውቋል።

የሳይበር ምሕዳር በባህሪው ድንበር የለሽና -ተገማች በመሆኑ ዓለም በዚህ መጠነ-ሰፊና ተለዋዋጭ ወንጀል በየቀኑ በአማካይ 16 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ሀብት ታጣለች።

የሳይበር ወንጀል 2015 በዓለም ላይ 3 ትሪሊየን ዶላር ካደረሰው ኪሳራ በእጅጉ እያንሰራራ መጥቶ 2021 ደግሞ 6 ትሪሊየን ዶላር አሳጥቷል።

በየዓመቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው ዓለም አቀፍ የሳይበር ወንጀል 2025 10 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሊያሳጣ እንደሚችል ተገምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰሞኑን በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 5 ሺህ 860 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓለም ላይ በየቀኑ በቢሊዮን ዶላር የሚያሳጣው የሳይበር ጥቃት ለኢትዮጵያም ፈተና መሆኑን ማስረዳታቸው ይታወሳል።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ፤የሳይበር ወንጀል በኢትዮጵያም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ።

በዚህም 2011 . 790 2012 . 1 ሺህ 80 2013 . 2 ሺህ 900 የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።

በዘንድሮው በጀት ዓመት 11 ወራት ደግሞ 6 ሺህ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ላይ የተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከየት እንደተሞከሩና የወንጀሉን ባለቤቶች በቀላሉ ለመለየት ባይቻልም ያነጣጠሩባቸው ተቋማት መለየታቸውንም ጠቁመዋል።

በሳይበር ጥቃቱ በተለይም በባንክና የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ማነጣጠሩን ጠቅሰው፤የሚዲያ ተቋማትም ኢላማ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

የመንግሥት ቁልፍ መሰረተ-ልማቶች፣የፖለቲካ አደረጃጀቶች፣ የፌደራልና የክልል የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም የጤና እና የትምህርት ተቋማትም በርከት ያለ ጥቃት ተሞክሮባቸዋል ተብሏል።

ከተሞከሩ 6 ሺህ የሳይበር ጥቃቶች መካከል 97 በመቶ በላይ ሙከራዎችን በማክሸፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል።

ሊደርስ የነበረውን አደጋ የማዳን አቅም እየጎለበተ መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ የሳይበር ወንጀል ሁልጊዜም -ተገማች በመሆኑ መጠንቀቅ እንደሚገባ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለምክር ቤቱ በሰጠቱት ማብራሪያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመደበኛ የሰራዊት ግንባታ ጎን ለጎን የሳይበር ጥቃትን የሚከላከል አቅም መገንባት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።