ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅም ወደፊት የሚያሻግር ነው!

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን 13 አመት ምክንያት በማድረግ በግድቡ ወቅታዊ ሁኔታ እና ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም ጋር በተያያዘ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢመደአ /ዋና ዳይሬክተር / አስቴር ዳዊት እንዳሉት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሀይል በማመንጨት ኦኮኖሚያዊ ጥቅም ከማስገኘቱም ባሻገር  በቀጠናው ላይ የሚኖረንን ተጽእኖ  እና አቅም  ወደፊት ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ኢመደአ በሳይበር  ምህዳር ላይ የሀገሪቱን ሉአላዊነት  ከማስጠበቅ ባለፈ በዋና ዋና ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ የራሱን አስተጽኦ  የሚያበረክት ተቋም መሆኑን የጠቆሙት / አስቴር እንደ ተቋም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ  መጠናቀቅ የምናበረክተውን ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ታላቁ  የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከመነሻው ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ደረጃ ያለውን ሂደት በሰፊው አብራርተዋል፡፡

በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት በተለይም በግብጽ ግድቡ ሲጀመር የነበረው የማደናቀፍ ዘመቻና ፕሮፓጋንዳ አሁን ላይ ወሳኝ በሚባል መልኩ መቀየሩን የተናሩት ፕሮፌሰር ያዕቆብ፤ የግድቡ መጠናቀቅና ስራ መጀመር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሀገራትም ጭምር በርካታ ጥቅሞችን የሚያስገኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

የህዳሴዉ ግድብ ጉዳይ ብዙ የዲፕሎማሲ ዉጣ ዉረዶች እንደነበሩት የገለጹት ፕሮፌሰሩ በዚህ ሂደት ዉስጥ ኢትዮጵያ ምክንያታዊ በሆኑ መከራከሪያዎች አሸናፊ ሆና መዉጣቷን ጠቁመዋል።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት 95% የደረሰ ሲሆን ግንባታው 2017 . ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅና የሃገራችንን የሃይል አቅርቦት ተደራሽነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚወስደዉ ይጠበቃል። 

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች