ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጋራ ለምስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የኢመደአ /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ እና የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ

ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋ ፈርመዋል፡፡

የኢመደአ /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የተሰጠውን ግዙፍ ሐገራዊ ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋ  በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል ጠንካራና ብቁ የባሕር  ኃይል በመገንባት ሂደት ውስጥ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በዛሬ እለት የተካሄደው ስምምነት  የኢትዮጵያ ባሕር ኃይልን ሁለንተናው አቅም ለማጎልበትና የማድረግ አቅሙን ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች