የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ 1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለኢመደአ የእስልምና እምነት ተከታዮች 1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት የሚከበረው የዒድ አልፈጥር በዓል የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመረዳዳት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት ያሳየውን የመረዳዳትና የመተዛዘን ድንቅ እሴት በማስቀጠል ለተቸገሩና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለዉን በማካፈል በዓሉን አንድ ሆነን በደስታና በፍቅር ልናከብር ይገባል ሲሉ / ትዕግስት ሃሚድ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ጠቁመዋል።

የታላቁን የዒድ አልፈጥር በዓል  ስናከብር  ህዝበ ሙስሊሙ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖቻችን ያለንን በማካፈል፣ ከጎናቸዉ በመቆምና በመደገፍ፣ በአብሮነትና በመተሳሰብ ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸዉን  አስተላልፈዋል።

ዒድ ሙባረክ!