የቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የቴክኖሎጂ እድገትና ምጥቀትንን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ አባል ሃገራት በትብብርና ቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ በሩሲያ በተካሄደዉ 10ኛዉ የብሪክስ አባል ሃገራት Working Group መድረክ ላይ ተናገሩ።

10ኛዉ የብሪክስ የወርኪንግ ግሩፕ ስብሰባ ‘Security in the use of Information and Communications Technologies’ በሚል ርዕስ ሁሉም የብሪስክስ አባል ሃገራት የዘርፉ ሃላፊዎች በተገኙበት ከአፕሪል 16-17 በሞስኮዉ  ሩሲያ እየተካሄደ ሲሆን በጉባኤዉ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስትና ልዑካቸዉ ተሳትፎ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከጃንዋሪ 1/2024 ወዲህ የብሪክስ አባል ሃገር መሆኗ ይታወቃል።

በዚሁ መድረክ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያከናወነች ያለዉን ተግባራት ያነሱት / ትዕግስት ብዙ ወጣት የሰዉ ሀይል እንዳላት ሀገር ኢትዮጵያ የወጣቱን ተሰጥኦ እና የፈጠራ ስራ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ የራሱን ሚና እንዲወጣ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በመድረኩ አንስተዋል።

በፍጥነት ከሚለዋወጠዉ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ጋር ራሳችንን በፍጥነት ማላመድና እኩል መጓዝ ካልቻልን የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከሚመጣዉ የሳይበር ጥቃት አደጋ ማንም ሊጠብቀን አይችልም ብለዋል። 

በአሁኑ ሰዓት የብሪክስ ሀገራትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የዓለም ሃገራት የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ዋና ጉዳያቸዉ ማድረጋቸዉን ያነሱት / ትዕግስት የኢንፎርሜሽን ደህንነት ጉዳይ በቀጣይም የብሪክስ አባል ሃገራትም ወሳኝ የዉይይት አጀንዳ ሆኖ መቀጠል እንደሚገባዉ ጠቁመዋል።

ሃገራት በሳይበር ምህዳሩ ላይ ትብብርና ቅንጅቶችን ማጠናከር አማራጭ የሌለዉ ምርጫችን ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የብሪክስ አባል ሃገራት የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን የመቋቋም አቅማቸውን በማጠናከር የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፋዊ ዲጂታል አካባቢን መፍጠር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

10ኛዉ የብሪክስ የወርኪንግ ግሩፕ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ አባል ሀገራቱ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ደህንነት፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል፣ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ለማከናወን፣ የሳይበር ጥቃትን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም የተሻሉ ልምዶችን ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

/ ትዕግስት ከመድረኩ ጎን ለጎን ከተለያዩ የብሪክስ አባል ሃገራት ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ዉይይቶችን አድርገዋል።