ኢመደኤ ለሚዲያ ተቋማት የዲጂታል ሚዲያ ላይ ስለሚፈጠሩ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ ለድረ-ገጽ፣ ለማህበራዊ ሚዲያ እና ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሙያተኞች በዲጂታል ሚዲያ ላይ ስለሚፈጠሩ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናዉ መክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ ለሳይበር ጥቃት መጋለጥ ዋነኛው መንስኤ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ያለን ግንዛቤና አረዳድ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ስለሳይበር ደህንነት ያለውን ንቃተ-ህሊና በማሳደግ በኩል የመገናኛ ብዙሃን ሚና ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ኃላፊዉ በተለይም የሚዲያ ተቋማቱ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በኩል የጎላ ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል፡፡

ከዚህ በለፈም መገናኛ ብዙሃን ራሳቸው ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጡ ስለሳይበር እና የሳይበር ደህንነት ምንነት፣ ባህሪያት፣ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች በአግባቡ ማወቅና መረዳት እንዳለባቸው ዶ/ር አንተነህ አሳስበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በየጊዜው እየጨመሩ የመጡ የሳይበር ጥቃቶች የሚያሳዩን በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት መበራከታቸውን እና እንደሀገር ችግሩን የሚመጥን ቅድመ ዝግጅት ካልተደረገና ዘላቂ መፍትሄ ካልተቀመጠ በሀገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ልንገነዘበው ይገባል ሲሉ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በኢመደኤ የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኃይሉ በማህበራዊ ሚዲያ ባህሎች፣ የደህንነት ስታንዳርዶች፣ ፖሊሲና መመሪያዎች፣ በመረጃ መታወክ ምንነትና እና የመፍትሔ እርምጃዎች ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

ከገለጻው በኋላ በተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረክ ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን ተሳታፊዎቹ በኢመደኤ የተዘጋጀውን አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡