ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ እና ኢጋድ በትብብር በሚስሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ መከሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 17/2014: የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ (ኢመደኤ) እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት (IGAD) በጋራ በሚስሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረጉ።

በዉይይቱ ላይ የተገኙት የኢመደኤ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸዉ ወርቁ ኤጀንሲዉ ከኢጋድ ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አንስተዉ በይበልጥ በምርምርና ልማት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በሳይበር ደህንነት ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ኢመደኤ እየሠራቸው ስላሉ ሥራዎች እና በትብብር ሊሠራባቸው በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለልዑክ ቡድኑ ሰፊ ገለጻ ተደረጓል።

በኢጋድ በኩል በኤጀንሲው የተገኙት የኢጋድ የደህንነት ዘርፍ ሃላፊ ኮማንደር አበበ ሙሉነህ በበኩላችዉ ኢጋድ በሰዉ ሃይል ማብቃት፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማማከር ዘርፍ ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የልዑክ ቡድኑ የተቋሙን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ እና አውደርዕይ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።