ተቋማት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ የሚዳርጓቸውን ጉዳዮችን በመለየት ከፍተቶችን የመድፈን፣ የባለሙያዎችን የሳይበር ግንዛቤ አቅም በማሳደግና በጋራ በመስራት የኢትዮጵያን የሳይበር ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ይጠበቅባቸዋል: ወ/ሮ ትግስት ሃሚድ፡ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ለሃገር ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1/2015 እስከ ጥቅምት 30/2015 ዓ/ም ድረስ እየተካሄደ የሚገኘው 3ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የ2ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የ2ኛ ሳምንት የሳይበር ደህንነት ወር ዋና ጭብጥ የተቋማትን የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት መቀነስ (Reducing Organizational Vulnerabilities) የሚል ሲሆን፤ በዚህም ተቋማት የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለባቸው የሚል ሰፊ ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የ2ኛ ሳምንት የሳይበር ደህንነት ወር መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሃሚድ እንዳሉት ተቋማት ወደ ውስጣቸው በመመልከትና ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ የሚዳርጓቸውን ጉዳዮችን በመለየት ከፍተቶችን የመድፈን፣ የባለሙያዎችን የሳይበር ግንዛቤ አቅም በማሳደግና በጋራ በመስራት የኢትዮጵያን የሳይበር ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሯ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፤

  • በአለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ እና የበይነመረብ በተለይም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ የቴክኖሎጂ ጥገኛ ሆነናል።
  • ምንም እንኳን የዲጂታል ምህዳሩን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ማደግ የዘመናችን አዲስ የህይወት እውነታ ሆኖ ቢገኝም፤ ተቋማት ስለ ሳይበር ደህንነት ያላቸዉ ግንዛቤ እጥረት እና የትኩረት ማነስ መንግስታትን ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ከቷቸዋል።
  • እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወደ ዲጂታል ምህዳሩ በቅርቡ በስፋት እየገቡ ያሉ ሀገራት  የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ በተቋም ደረጃ ያለዉ የግንዛቤ ክፍተትም  በየአመቱ እያደጉ ለመጡት የሳይበር ጥቃቶች የመሪነት ሚናን እየተጫወተ ነዉ።
  • ተቋማቶቻችን ላይ የሚፈጸም የትኛዉም አይነት የሳይበር ጥቃት በተቋሞቻችን የስም ማጥፋት፣ የገቢ መቀነስና ኪሳራ ባሻገር ተቋሞቻችንን እስከመጨረሻዉ ሊያሳጣን ይችላል።
  • የላቁ ቴክኖሎጂዎችን እና መተግበሪያዎችን በቀላሉ የማወቅ እና የመረዳት እንዲሁም ቶሎ የመቀበል አቅም በሳይበር ዓለም ውስጥ ተቋማት ተፎካካሪ ሆነዉ ለመቀጠል ወሳኝ የሆነበት ወቅት ላይ ነን።
  • ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ 82 ከመቶ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸዉ መተግበሪያዎች የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ያለባቸዉ ናቸዉ።
  • መንግስታዊም ሆኑ የግል ተቋማት የሚጠቀሙባቸዉ ቴክኖሎጂዎች እና የአሰራር ስርዓታቸዉን ማዘመን፣ የቁጥጥር እና ክትትል ስርዓታቸዉን ማስፋት፣ ዘመኑን የሚመጥንና ደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን እና በመጠቀም በተቋማትና በሃገር ላይ ሊደርስ ከሚችል የሳይበር ጥቃት በጋራ መከላከልና መጠበቅ ይገባናል።

3ኛዉን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ስናከብር፤ ተቋማት ወደ ውስጥ በመመልከትና ለሳይበር ተጋላጭነት የሚዳርጉ ጉዳዮችን በመለየት ከፍተቶችን የመድፈን፣ የባለሙያዎችን የሳይበር ግንዛቤ አቅም በማሳደግና በጋራ በመስራት የኢትዮጵያን የሳይበር ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ።