የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ ቴክኖሎጂዎችን በራስ አቅም ማልማትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 07/2017 ዓ.ም፡- በዲጂታል ዓለም ውስጥ በአርበኝነት ስሜት የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ ቴክኖሎጂዎችን በራስ አቅም በማልማትና በማበልጸግ መጠቀም እንደሚገባ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ቢኒያም ማስረሻ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ በዛሬዉ ዕለት በይፋ ባስመረቀበት ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት "ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የዲጂታል ሚዲያው ሚና ምንድን ነው" በሚል ርዕስ የመነሻ ፅሁፍ በአቶ ቢኒያም ቀርቧል።

በዲጂታል ዓለም ውስጥ ሆነን የዲጂታል ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ ካልተቻለ ለጥቃት ተጋላጭነታችን እየሰፋ ይሄዳል ያሉት አቶ ቢኒያም አሁን ባለው ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቴክኖሎጂን በራሳችን አቅም ማልማትና መጠቀም እስካልቻልን ድረስ ጥገኛ እንሆናለን ያሉት አቶ ቢኒያም፤ የዲጂታል ጥገኝነት እስካለብን ድረስ የሉዓላዊነት ጉዳይ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አንስተዋል።

በፓናል ዉይይቱ ወቅት የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል አንድ ተቋም ቴክኖሎጂውን የሚያስተዳድርበት የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ አደረጃጀት፣ መሰረተ ልማቱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ረገድ ያለበት ደረጃ፣ የሰለጠነ ባለሙያ፣ የንቃተ ህሊና ፕሮግራም እንዲሁም የዓለም አቀፍ ስታንደርድ መስፈርቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።