ኢመደአ እና የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ፈረሙ።

በስምምነቱ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሀገራችንን የስኳር ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ለዉጭ ገበያ ለማቅረብ በሚያደርጋቸዉ ጥረቶች ኢመደአ በራሱ አቅም ባለማቸዉ ቴክኖሎጂዎችና የሰዉ ሀይሉን በማሰልጠን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዋዮ ሮባ በበኩላቸዉ አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለዉን የስኳር ፍላጎት ለመሽፈን በተለምዷዊዉ አካሄድ መሄድ አዋጭ አለመሆኑን በመረዳት ተቋማቸዉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ መጠቀም መምጣቱን ገልጸዋል።

ይህን ቴክኖሎጂ ደግሞ እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በመሳሰሉ በዘርፉ የካበተ ልምድ ካላቸዉ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከመግባቢያ ስምምነቱ ባሻገር የኢመደአን ምርትና አገልግሎቶችን እንዲሁም የኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕከልን ጎብኝተዋል።