እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና የአስተዳደሩ አባላት 1 ሺህ 500ኛውን የነብዩ መሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ወ/ሮ ትዕግስት በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ በዓሉ ሲከበር የነብዩ መሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) በረከቶች በማስተዋል መንገዳቸውን በማሰብ እና መልካም ሥራቸውን በማየት መሆን ይገባል ብለዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙም በዓሉን ሲያከብር አቅም የሌላቸውን በመጎብኘትና ካለው በማካፈል መሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የዘንድሮዉን የመዉሊድ በዓል የምናከብረዉ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮና ሁለተኛዉ አድዋችን በሆነዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በራስ አቅምና ሃብት ገንብተን በጨረስንበት ወቅት መሆኑ በዓሉን እጥፍ ድርብ እንደሚያደርገዉ ጠቁመዋል።
ከዚህ በመለስ በበዓል ወቅቶች የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ከፍ እንደሚሉ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ የበዓላት ግርግር ለአጭበርባሪዎች ምቹ በመሆኑ የሳይበር ወንጀለኞች የባንክ ቤቱን ወረፋ፣ የሰዉን ጥድፊያ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኦንላይን ጥቃት እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል።
በመሆኑም ዜጎች የበዓል ሽመታዎችን ሲያደርጉ፣ የበዓል ጉዞን ሲያድርጉ፣ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ፣ ክፍያዎችን ሲፈጽሙ፣ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሲለግሱ ወ.ዘ.ተ በአጭበርባሪዎች ወጥመድ ሊወድቁ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የ2017 ዓ.ም የመውሊድ በዓል ለኢመደአ ማህበረሰብ እና ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን የሰላም፣ የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸዉን ገልጸዋል።