ኢመደአ፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በጋራ በመሆን የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄዱ፡፡
ኢመደአ፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በጋራ በመሆን የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄዱ፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሰላም ሚኒስቴር፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በጋራ በመሆን የኢፍጣር መርሐ- ግብር አካሄዱ፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሃመድ ኢድሪስ፣ የአርተፍሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና፣ እንዲሁም ሚንስትር ዴታዎች፣ የተቋማቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ መካከለኛ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በመርሃ ግብሩ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዬ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ዋና ጸሃፊ ሼህ ሃሚድ ሙሳ፣ ኡስታዝ በድሩ ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል።
ከኢፍጣር መርሃ ግብሩ ጎን ለጎን ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አከናዉኗል።