የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር የተቀናጀ ዲጂታል የመሬት ምዝገባ እና ተያያዝ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የውል ስምምነቱ ከመሬት ምዝገባ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ዲጂታይዝ የማድረግ ሥራ፣ ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት (online services) የዲጂታል ክፍያ የካዳስተር ሥራ፣ የመሬት ምዝገባን ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር የማስተሳሰር፣ በከተማው ያለን የመሬት ሀብት መረጃ ሲስተም የመዘርጋት፣ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ፣ የመረጃውን ደህንነት የመጠበቅና ባለሞያዎች በራሳቸው መጠቀም እንዲችሉ ስልጠና የመስጠት ስራዎችን የያዘ ሲሆን  20 ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልጿል፡፡ 

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ደህንነቱ የተጠበቀ ስማርት ሲቲን እውን ለማድረግ የሚያስችል ሲስተም አበልጽጎ የሚያስረክብ ሲሆን ይህ ሲስተም ለአሥተዳደር ምቹ፣ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል፤ መንገድ፣ መብራት፣ ውኃ፣ የፖሊስ ሥራን የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያሳልጥ፤ ለዜጎች ምቹና ማራኪ የሆነ ኢንቨስትመንትን የሚጋብዝና ምርታማነትን የሚጨምር፤ ስማርት ከተማ መመስረት የሚያስችል ሲስተም ስንገነባ ይህ ሲስተም ደህንነቱ እንዲጠበቅ በዘላቂነት በትብብር እንሠራለን ብለዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቴክኖሎጂን ከማዘመን አኳያ የከተማው አስተዳደሮች ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ እንዲሆኑና ፕሮጀክቱን በየጊዜው በቅርበት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ / ተሾመ አዱኛ በበኩላቸው እንዳሉት ሸገር ከተማን የወደፊት  ስማርት ከተማ ለማድረግ የተያዘውን አላማ ለማሳካት የመሬት ምዝገባ /የካዳስተር/ ስራዎች ቁልፍ መሆናቸውን ገልጸው፤  ከዚህ ቀደም በከተማዋ የሚታየውን ያልተደራጃ እና  የተበጣጠሰ የመሬት አስተዳደር ስርአት ወጥ ወደ ሆነ  እና በቴክኖሎጂ በታገዘ  መልኩ በመስራት እና  ከተማውን የወደፊት ስማርት  ከተማ  ለማድረግ የያዝነው ራእይ ለማሳካት  እንደ ኢመደአ አይነት በዘርፉ እውቀት እና ልምድ  ካለው ተቋም ጋር መስራታችን ራእያችንን እውን ለማድረግ ያስችለናል  ብለዋል ፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች