ኢመደአ እና ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

በዉይይቱ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ የጋራ ውይይቱ ሁለቱም ተቋማት በሃገር ደረጃ ከተሰጣቸው ኃላፊነት አንጻር በመደመር ፍልስፍና በጋራ መስራት ትልቅ እድል ነው ብለዋል።

በተለይም ኢመደአ በሳይበር ደህንነት እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም ኮሚሽኑን ሃገር በቀል ቴከኖሎጂዎችን በማስታጠቅ ፣ በስልጠናና ማማከር ብሎም በሌሎችም ዘርፎች ያሉንን የጋራ አቅሞች በመለየት ለሃገራችን እድገት ፣ ሰላምና ብልጽግና መስራት ይገባናል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ከኢመደአ ጋር በጋራ ሃገራዊ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ ትልልቅ ጉዳዮችን በመለየትና በጋራ በመስራት ውጤት ማምጣት የሚቻል መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ለመገንባት አጋዥ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማስታጠቅና እየተጠቀምንባቸው ያሉ ሲስተሞችን ደህንነት በማረጋገጥ በኩል ከኢመደአ ጋር በጋራ መስራታችን ጠቃሚ ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ኢመደአ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ ኮሚሽኑ ሁሉን አቀፍ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በዉይይቱ ኢመደአ ባለው የቴክኖሎጂና የሳይበር ደህንነት አቅም ለኮሚሽኑ ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር እንዲገነባ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን የማስታጠቅ ስራዎችን ለማከናዎን የሚያስችል ስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታ (Road-map) በማዘጋጀት በቀጣይ አብረው በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ መግባባት ተደርሷል።

በውይይቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ጨምሮ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የስራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል::

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች