ኢመደአ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሁለት አረጋዊያንን ቤት አድሶ አስረከበ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በሰው ተኮር ማህበራዊ በጎ አድራጎት መርሃ ግብር የሁለት አረጋዊያንን ቤት አድሶ አስረክቧል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት እንደገለፁት ኢመደአ ከተሰማራበት ሃገራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን ሰው ተኮር የሆኑ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በመወጣት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ አስተዳደሩ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣቱ ጋር በተያያዘ በእለቱ የተደረገው የርክክብ መርሃ ግብር አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ኢመደአ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ም/ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ አስቴር ጠቅሰዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ከድር በበኩላቸው ኢመደአ በሀገራዊ ሪፎርም ሞዴል ከሚደረጉ ተቋማት እንዲሁም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ቀዳሚ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አይይዘውም ዶ/ር ብሩክ እንዳሉት ክፍለ ከተማው በያዘው የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው የአቅመ ደካሞች ቤትን ማደስ መርሃ ግብር ኢመደአ የአቅመ ደካሞችን ቤት አድሶ በማስረከቡ ምስጋናቸውን ገልፀው፤ ይህም ተግባር ለሌሎች ተቋማትም በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ደሳለኝ ባዳረጉት ንግግር ኢመደአ በወረዳቸው ፈርጀ ብዙ እገዛ እያደረገላቸው እንደሆነ አስታውሰው፤ ለዚህም ለአስተዳደሩ የምስጋና የምስክር ወረቀት በእለቱ ለተገኙት ለኢመደአ ከፍተኛ አመራሮች አበርክተዋል፡፡

ቤታቸው ታድሶ ከሙሉ የቤት መገልገያ ቁሳቁሶች ጋር የተረከቡት አራጋዊያን እናቶች በበኩላቸው በተደረገላቸው ድጋፍ እና እገዛ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢመደአ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የቢሮ ቁሳቁሶች (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ ዩፒኤስ፣ ተሽከርካሪ ወንበር፣ ጠረጴዛ እና ሌሎቸ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች) ጨምሮ ከዛሬው የቤት እድሳት ጋር ከ4.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡