የዲጂታል ሉአላዊነት ጉዳይ የአንድ ሀገር ብሄራዊ ሉአላዊነት ጉዳይ ሆኗል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

ኢትዮጵያ የራሷ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለማልማት የያዘቸው አቋም በቴክኖሎጂው ዘርፍም ነፃ ሀገር መሆኗን ለማሳየት የታሰበ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢመደኤ) / ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

/ ሹመቴ አክለውም የዲጂታል ሉአላዊነት ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን ያነሱ ሲሆን፤ዘግየት ብለን ወደ ዘርፉ እየገባን ያለን ሀገራት በጣም በጥንቃቄ መግባት አለብንብለዋል።

የዲጂታል ሉአላዊነት ጉዳይ የአንድ ሀገር ብሄራዊ ሉአላዊነት ጉዳይ እስከመሆንም ደርሷልያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤የራሳችንን እና ተቋሞቻችንን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ ሲቻል የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነምአክለው አንስተዋል።

በሳይበር ምህዳሩ ላይ የሀገርን ሉአላዊነት ማስጠበቅ ደግሞ ለአንድ ቡድን አሊያም ተቋም የሚተው ሳይሆን፤ የሁሉም ኃላፊነት እና የየእለት ስራ መሆኑን አስታውቀዋል።

የማህበራዊ ትስስር እና የተግባቦት (ኮሙዩኒኬሽን) መተግበሪያዎችን ከማልማት ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ያላት አቋም ሌሎችን በመዝጋት ሳይሆን አማራጭ የሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ማቅረብ አለብን የሚል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነችያሉት / ሹመቴ፤ነጻ ሀገር ሆነን ቆይተናል፤ በቴክኖሎጂው ዘርፍም ነጻነታችንን ማሳየት አለብን በሚል እሳቤ ነው እየተሰራ ያለውሲሉም ተናግረዋል።

የተግባቦት መተግበሪያዎችን አሁን ላይ ለምተው እና ሙከራ ተደርጎባቸው የተወሰኑ ተቋማት ብቻ የሚጠቀሙባቸው አሉ ያሉ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍም በራስ አቅም እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን እና ውጤት ማስገኘታቸውንም አስታውቀዋል።

ሆኖም ግን መተግበሪያውን ማልማት ብቻ በቂ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከመተግበሪያዎቹ ጀርባ ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ያስፈልጋሉ፤ ለዚህም መንግስት ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ ስለመሆኑም ገልፀዋል።

አሁን ላይ ግን ለመጠቀም የደረሱ የተግባቦት (ኮሙዩኒኬሽን) ፕላትፎርሞች መኖራቸውን በማንሳት፤ ባልራቀ ጊዜ ውስጥ ለህዝቡ ይፋ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉም ተናግረዋል።

እንደ ፌስቡክ እና ትዊት ያሉ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ እያራመዱ ያሉትን አቋም በተመለከተ / ሹመቴ፤በድረ-ገጾቹ ባለቤቶች እና እዛ ውስጥ ባሉ ተዋናዮች እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ሆን ተብሎ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ወዳጆች እያጠቁ እንደሆነ ይታወቃልብለዋል።

አሁንም ቢሆን ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ መልእክቶች የሚተላፉባቸው ገጾችን መዝጋታቸውን ቀጥለውበታል፤እኛ ኢትዮጵያውያን ነን፤ በቴክኖሎጂ አመጣሽ ሽብር አንሸነፍምሲሉም ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ከፌስቡክ ጋርም ይሁን ከትዊተር ጋር ብዙ የምንነጋገርባቸው በርካታ ነገሮች አሉ፤ እንነጋገርበታለንሲሉም ተናግረዋል።

የቴክኖሎጂ ውጤቶች የነሱ ናቸው፤ ስለዚህ እኛ ሄድንባቸው እንጂ እነሱ አልመጡብንም ያሉት / ሹመቴ፤ ስለዚህ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የራሳችን የሆነ ገጾችን እናዘጋጃለንብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሀሳቦች ያላቸው በግልም ይሁን በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ያሉ አካላት ወደ ኢመደኤ በመምጣት በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።