የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የገቢዎች ሚኒስቴር የውል ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) “የኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአት - Ethiopian Electronic Invoice Administration System” እንዲሁም የዳታ ዌርሃውስና ቢዝነስ ኢንተለጀንስ ሲስተም ለማልማት የሚያስችል የውል ስምምነት ከገቢዎች ሚኒስቴር  ጋር ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሃሚድ እና የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት / አይናለም ንጉሴ ፈርመዋል፡፡

በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹትየኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአትበዋናነት በሐገራችን ያለውን የማንዋል የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ወደኤሌክትሮኒክስ የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ለመቀየር የሚያስችል እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ስርአቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳልጥ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ከዚህ ቀደም በካሽ ሬጅስተር ማሽን (Cash Register Machine - CRM) ሲሰጥ የነበረውን የደረስኝ ስርአት ከማገዝ ባሻገር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጨማሪ አቅም በመፍጠር  የታክስ አስተዳደር ስርአት ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው / ትዕግስት ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሐገራችንን የሳይበር ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር ለዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ የሆኑ ስርአቶችን በማልማት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የራሱን ሚና እንደሚጫወት / ትዕግስት ገልጸዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሐገራችን የሚስተዋለውን በሃሰተኛ ደረሰኝ የማጭበርበር እና የታክስ ስወራ ከማስቀረት አኳያየኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአትወሳኝ ሚናን የሚጫወት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘው እንደተናገሩት ስርአቱ የግብይት ደረሰኝን ከአንድ አካል ብቻ ማለትም ከገቢዎች ሚኒስቴር ብቻ እንዲቆረጥ በማድረግ በሃሰተኛ ደረሰኝ የሚደረግ ማጭበርበርን የሚያስቀር ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአትለነጋዴው ማሕበረሰብም ሆነ ለሸማቹ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ እንደሆነ የተናገሩት / አይናለም፤ የነጋዴው ማህበረሰብ ለደረሰኝ ሕትመት የሚያወጣውን ወጪና ጊዜ ከማስቀረቱም በላይ የግብይት ሂደቱን በቀጥታ ለመከታተልና ለመቆጣጠርም ያስችለዋል ብለዋል፡፡

በሌላም በኩል የሸማቹ ማሕበረሰብ የሚከፍለውን ተደራራቢ ታክስ ከመቀነስ እንዲሁም ላከናወነው ግብይት ትክክለኛ ደረሰኝ ከማግኘት አኳያ ስርአቱ ትልቅ ፋይዳ እንደሚሰጥ / አይናለም አብራርተዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች