የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር “በሩት ሰርተፍኬት” ሰጪ ባለስልጣንነት ሚናው ለሚሰጣቸዉ የተለያዩ አገልግሎቶች ተመጣጣኝ ክፍያ እንዲያስከፍል የሚኒስትሮች ምክርቤት ዉሳኔ አሳለፈ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 10/2014 ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው አስተዳደሩ ሩት ሰርተፍኬት ባለስልጣን በመሆን ለሚሰጣቸዉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ ክፍያዎችን ጋር በተያያዝ ዉሳኔ አሳልፏል።

ወሳኔዉ በበይነ-መረብ እና በኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የሚደረጉ ግንኙቶች ላይ መተማመን መፍጠር የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ዲጅታል ፊርማ ሲሆን ዲጅታል ፊርማ ዋና ዋና የደህንነት ጉዳዮች የሆኑትን ሚስጥራዊነት መጠበቅ፤ የላኪና ተቀባይ ትክክለኛ ማንነት ማረጋገጥ፣ የዳታ ትክክለኛነት እና ኦሪጅናሊቲ መጠበቅ እና መካካድ ማስቀረት የማስቻል አቅም አለው።

ዲጂታል ፊርማን ተግባራዊ ለማድረግ በዋናነት አራት የማይነጣጠሉ አሃዶች (components) የሚያስፈልጉ ሲሆን እነዚህም፡-ቴክኒካዊ መፍትሄዎች፣ የክሪፕቶ መሰረተ ልማት፣ የህግና የቁጥጥር ማእቀፎች እንዲሁም ተቋማዊ አደረጃጀት ናቸው።

በክሪፕቶ መሰረተ ልማት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው ሞዴል ተዋረዳዊ አወቃቀር በመሆኑ ህጉ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጁ ሲዘጋጅ አስተዳደሩን ሩት ሰርተፍኬት ባለስልጣን በማድረግ መውጣቱ ይታወሳል።

በዚህ መሰረትም የክሪፕቶ መሰረተ ልማቱ አዋቃቀር የፖሊሲ እና የሬጉላቶሪ ስራዎችን የሚሰራ “ሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን” እና በስሩ ደግሞ መሰረተ ልማቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ “ሰርተፊኬት ሰጪዎች” የሚኖሩት ሆኖ የወጣ መሆኑ ይታወቃል።

ቀደም ሲል ዲጅታል ፊርማን አስመልክቶ በኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ስፊ ሽፋን ተሰጥቶት ወጥቷል።

በዚህ አዋጅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሩት ሰርተፍኬት ባለስልጣንነቱ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባራት መካከል ለሰርተፍኬት ሰጪነት የሚያበቃ ፈቃድ የመስጠት፣ የፍቃድ መስፈርቶች ማውጣት፣ ሰርተፍኬት የማገድ፣ ፈቃድ የመሰረዝ፣ ለውጭ ሰርተፍኬት ሰጪዎች እውቅና የመስጠጥ እና የሰርተፍኬት ሰጪዎች አጠቃላይ አሰራርና ደህንነት ኦዲት የማድረግ እና ተያያዥ ተግባራት ናቸው።

በተጨማሪም በአዋጁ ቁጥር 1072/2010 አንቀጽ 11(3) ሩት ሰርተፍኬት ባለስልጣን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ክፍያ እንደሚያስከፍል ተደንግጓል። በዚህም መሰረት የክፍያ ዋጋው ሲተመን የሌሎች ሃገራት ልምድ፣ ሩት ሰርተፍኬት ባለስልጣኑ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጣውን ወጪ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን ማበረታት እና ዘርፉን የማሳደግ አላማን ከግንዛቤ በመክተት ተቀምጧል።

በሃገራችን ዘርፉ በዋናነት ለሃገር ውስጥ ባለሃብት ክፍት የተደረገ በመሆኑ እና የዘርፉ መስፋፋት የሃገሪቱን የዲጂታላይዜሽን ሂደት በዋናነት የሚደግፍ በመሆኑ ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ ለማስቀመጥ እና ከትርፍ ይልቅ ሩት ሰርተፍኬት ሰጪዎች ለሚያወጣው ወጪ መደጎሚያ በሚሆን መልኩ የአገልግሎት ክፍያ ዋጋው እንዲተመን ተደርጓል።

በዚህም መሰረት በአዋጁ እና አዋጁን ተከትሎው በወጡ ህጎች ላይ የተለዩ አገልግሎት አይነቶች ማለትም፡-የሰርተፍኬት ሰጪነት፣ አገልግሎት ፍቃድ፤ የሪፖዚተሪ አገልግሎት ፈቃድ፣ የጊዜ ማህተም አገልግሎት ፈቃድ፣ ለውጭ ሰርተፍኬት እውቅና መስጠት፣ ለውጪ ጊዜ ማህተም እና ለሪፖዚተሪ አገልግሎት እውቅና መስጠት፤ ፈቃድን ለማዘዋወር የሚከፈል ክፍያ የተለዩ ሲሆን እነዚህን አስመልክቶ የሚቀርቡ ማመልከቻ፣ የፈቃድ፣ የእድሳት፣ የምትክ ፈቃድ፣ እንዲሁም ኦዲት ለማድረግ የአገልግሎት ክፍያው በደንብ እንዲወጣ ተደርጓል።