“ድሮኖችን” ለሃገራዊ ልማት እና ለሰብአዊ አገልግሎት ለማዋል ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 18/2014: የሰዉ አልባ በራሪ ቁስ (drone) “ድሮኖን” ለሃገራዊ ልማት እና ለሰብአዊ አገልግሎት ለማዋል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሃገር አቀፍ ምክክር ተካሄደ።

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) መሪነት በአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP)አስተባባሪነት በተዘጋጀዉ ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ የሰዉ አልባ በራሪ ቁሶች “ድሮኖች” በሃገራት የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የጂኦፖሊቲካዊ ጉዳዮች ላይ ሚናቸዉ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የድሮን ቴክኖኦጂ በስፋት ወታደራዊ ተግባር ላይ በመዋል በስፋት ቢታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቴክኖሎጂዉ በሳይንስ ፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በጤና ጥበቃ፣ በመዝናኛ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኙ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ከዚህ ባሻገር የሰዉ አልባ በራሪ ቁሶች ወንጀለኛን ለመከታተል፣ የምርትና አቅርቦት ዘርፍን ለማጎልበት፣ የሰላም ማስከበር እና የአየር ላይ ፎቶግራፍ ለማንሳት ተግባራት በስፋት እየዋለ እንደሚገኝ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።

ሆኖም የድሮን ተጠቃሚነት ባደገ ቁጥር በህገ-ወጦች እጅ የመዉደቅ እድል ስላላቸዉ የሃገራት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ይሆናሉ ያሉት የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራትም ከሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚገኘዉን ጥቅም በአግባቡ ለማግኘት በሃገር አቀፍ ደረጃ የአጠቃቀም መመሪያ ፣ ፖሊሲ እና ህጎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ የምክክር መድረክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መሪነት የሰዉ አልባ አዉሮፕላኖችን ለልማት እና ለሰብአዊ ተግባራት ለማዋል ጉዳዩ የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ሃገራዊ ግብረ ሃይል ማቋቋምን ታሳቢ ያደረ ሲሆን በዚህ ግብረ ሃይል ዉስጥ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ባሻገር የአለም የምግብ ፕሮግራም በአስተባባሪንት የግብረ-ሃይሉ አካል ይሆናል።

የዚህ ሃገር አቀፍ ግብረ-ሃይል የማቋቋም አላማም የሰዉ አልባ ቁሶችን በሃገራዊ ልማት እና ለሰብአዊ ተግባራት ላይ የማስተባበር እንዲሁም የሰዉ አልባ በራሪ ቁሶች አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዝግጅት ላይ የመደገፍ እንዲሁም ህጎቹን ማስፈጸም ስራ የሚሰሩ ይሆናል።