የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ከሐምሌ 27/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒ ኤች ዲ) ተሾመዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከመሰረቱ ቀደምት ባለሙያዎች መካከል የነበሩ ሲሆን ከቴክኒካል ባለሙያነት ጀምሮ እስከ ምክትል ዳይሬክተርነት ለ10 አመታት ያክል ተቋሙን አገልግለዋል፡፡ በ2008 ዓ/ም ተቋሙን ከለቀቁ በኋላ “ቴክ ማሂንድራ” በተባለ የህንድ የመረጃ ቴክኖሎጂ አገልግሎት እና አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ሆነው ለስድስት ዓመታት ሰርተዋል።  

አቶ ሰለሞን ሶካ ከ 6 አመታት ቆይታ በኋላ ወደ ኢመደአ በመመስ ከህዳር ወር 2014 ዓ/ም ጀምሮ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው ከሐምሌ 27/2014 ዓ/ም ጀምሮ  የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል ፡፡

አቶ ሰለሞን ሶካ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በሶፍትዌር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን የማስተርስ ዲግሪያቸው ደግሞ ከቻይና ኤሌክትሮኒክ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አግኝተዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በሰኔ 2013 ዓ.ም በተካሄደው ስድስተኛው አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ የደቡብ ክልል ኮንሶ ዞንን ወክለው ተወዳድረው በማሸነፍ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራርና አባላትም ለአቶ ሰለሞን ሶካ መልካም የሥራ ጊዜን ይመኛሉ፡፡