የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የየተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት መምራት ይጠበቅብናል: ዶ/ር መኩሪያ ሃይሌ፡ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የ2ኛ ሳምንት የሳይበር ደህንነት ወር መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሃይሌ፡ የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የየተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት መምራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፤

  • ሀገራችን አምራች የሆነ የሰው ሀይሏን በመጠቀም ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንድታሳይ  ወጣቱን ትውልድ  የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እና ፈጠራ ላይ ብቃት እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤውና  አቅሙ እንዲዳብር በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት ያስፈልጋል፡፡
  • አብዛኛዎቹ የሀገራችን ተቋማትም ስራቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ከሚሰጡት ትኩረት አንጻር የቴክኖሎጂውን ደህንነት ለመጠበቅና ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት  እጅግ አነስተኛ መሆኑ አደጋው የሚያደርሰውን ጉዳት የከፋ ያደርገዋል፡፡
  • መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት  የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን ለማዘመን ከሚሰሩት ስራ ጎን ለጎን ለሳይበር ደህንነት ትኩረት በመስጠት በአሰራር ስርአት፣ በቴክኖሎጂ እና ብቁ የሰው ሀይል በመመደብ ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል።
  • በተለይም የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የየተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት መምራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በኢመደአ የተዘጋጀውን የሳይበር ወር  እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም  ተቋማት አመራሮቻቸውንና ሰራተኞቻቸውን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ለማሳደግ መሰል መርሀ ግብሮችን በራሳቸው ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል