የሀገራችንን የፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል የስራ ውል ስምምነት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መካከል ተደረገ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የሀገራችንን የፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓት በማዘመን ለዜጎች ቀልጣፋና ተደራሽ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የስራ ውል ስምምነት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና በፌዴራል ጠቅላይ /ቤት መካከል ተደረገ፡፡

በዛሬዉ ዕለት የተደረገዉ የስራ ዉል ስምምነት ከዚህ ቀደም በሁለቱ ተቋማት መካከል በመግባቢያ ደረጃ የተፈጸመዉን ስምምነት ወደ ዉል የቀየረና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ ነዉ።

ስምምነቱ በዋናነት የፌዴራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶችን የአሰራር ስርዓት ለማዘመን የሚያስችልየተቀናጀ የፍትህ ጉዳይ አስተዳደር ሲስተም" በመገንባት እንዲሁምኤሌክትሮኒክ የሰነድ አስተዳደር ስርዓት" ተግባራዊ በማድረግ አጠቃላይ የፍርድ ቤቶችን የአሰራር ስርዓት ማዘመንና ለዜጎች ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡  

ስምምነቱን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትና የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሃሚድ ፈርመዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በውል ስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት  “የተቀናጀ የፍትህ ጉዳይ አስተዳደር ሲስተምእናኤሌክትሮኒክ የሰነድ አስተዳደር ስርዓትበአንድ በኩል የፍርድ ቤቶችን የአሰራር ስርዓት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የሀገራችንን የፍትህ አሰጣጥ ስርዓት መሰረታዊ በሆነ መልኩ የሚቀይር ሲሆን፤ በሌላም በኩል ዜጎች በፍርድ ቤቶች አሰራር ላይ ያላቸውን እምነት እና እርካታ የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡

የሀገራችንን የፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል የውል ስምምነት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር መደረጉ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ አኳያም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ገልጸዋል፡፡    

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸዉ የሀገራችንን የፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓት ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለማዘመን የሚያስችል የሥራ ውል ስምምነት መደረጉ ለፍትህ ስርዓቱም ሆነ በአጠቃላይ ለዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን ሥራ በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸም ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል::

የፍትሕ ስርዓቱን ማዘመንና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ  የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከቀዳሚ ትኩረቶች መካከል አንዱ መሆኑንም / ትዕግስት ሃሚድ በስምምነቱ ወቅት ጠቁመዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች