አጥፊ ተልእኮ ባነገቡ ሊንኮች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች የትኞቹ ናቸዉ? እንዴትስ እንከላከላቸዉ?

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

አጥፊ ተልእኮ ያነገቡ ማስፈንጠርያዎች #Links በኢ-ሜይል ወይም በሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ይዘቶች ዉስጥ ተካተው (embedded) ሆነዉ የተለያዩ አጥፊ ሶፍትዌሮች (እንደ ቫይረስ፣ ትሮጃን፣ ራንሰምዌር፣ ወዘተ) ለማሳራጨት ታስበዉ የተፈጠሩ ናቸው።

እንዲሁም እነዚህ አገናኞች ወደ ሐሰተኛ ድረ-ገፅ በመምራት ለጥቃቱ ማስፈጸሚያ የታጩ አካላት ሚስጥራዊ መረጃዎን እንዲሰጡ የተለያዩ የማሳመኛ መንገዶች ይጠቀማሉ።

የዚህ አጥፊ ተልእኮ ካነገቡ መካከልም ስፓሞች፣ ፊሺንግ ኢ-ሜይሎች እንዲሁም ሀሰተኛ ድረ-ገፆች ዋነኛ መገኛ ሆነዉ እናገኛቸዋለን።

ነገር ግን አጥፊ ተልእኮ ያነገቡ ማስፈንጠሪያዎች (Links) በሐሰተኛ እና ሕጋዊ (Legitimate) ድረ-ገፆች ላይ ሊፈጠሩ ወይም ሊገኙ እንደሚችሉ ማስተዋል አስፈላጊ ነው።

ስለሆነም አጥፊ ተልእኮ ያነገቡ አገኛኞች ወይም ማስፈንጠርያዎች (Links) የሳይበር ወንጀለኞች ሳይበር ጥቃት ለማድረስ የሚስችሏቸው ውጤታማ መንገድ ሆነዉ አግኝተዉታል።

በአደገኛ ተልእኮ ባላቸዉ ሊንኮች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዉስጥም የሚከተሉትን ይገኙበታል፦

#የማንነት_ስርቆትን ወይም ሌሎች የማጭበርበር ተግባራትን ለመፈጸም፤

#_የግል_ሚስጥራዊ መረጃዎችን ወይም አካዉንቶችን መለያዎችን ለመድረስ #access ለማድረ፤

#_አደገኛ_ተልእኮ ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ለማውረድ፤

#_በራምሰምዌር አማካኝነት ፋይሎች ለመመስጠር ወይም ለመቆለፍ፤

#_በርቀት ሆነዉ ያልተፈቀደላቸዉን ስርአተ ኮምፒዉተር ለመቆጣጠር እና ለመበርበር ይጠቀሙበታል።

አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉን አገናኞች (link)እንዴት መከላከል እንችላለን?

ምንም እንኳ ደህንነታቸው የተጠበቀ አገናኞችን ከአጥፊዎቹ ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ሊተገሯቸው የሚገቡ የመከላከያ መንገዶች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል።  

  • ጠየቁት ወይም የማያውቁት ኢ-ሜይል አለመክፈት: በኢ-ሜይሎች፣ በጽሑፍ መልእክቶች ወይም Pop-ups ውስጥ የሚላክልዎት ሊንኮች በጭራሽ ማመን የለብዎትም። ምንም እንኳን መልእክቱ እና ሊንኮች ሕጋዊ ቢመስሉም ፤ ይህን ሊንክ  ከመክፈት ቆጠቡ ይገባል
  • ሊንኮች ላይ የኮምፒዉተር ማውዝበማቆየት በአስውሎት ይመልከቱ: (ያንዣብቡ) አንዳንድ ጊዜ አገናኞች የሚያገናኙትን አድራሻዎች ይዘዉ ይገኛል፤ አገናኙን  ከማፈላለጊያ  ጋር እየተመለከቱ ከሆነ በላዩ ላይ መቆየት (በማንዣበብ) የመረጃ ማፈላለጊያ ዩአርኤሉን በማየት አድራሻው እውነተኛ ወይም ሀሰተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።
  • https  ያላቸው ድረ-ገፆች ብቻ ይጠቀሙይህ ሁሉንም አይነት ግንኙነቶች (communications) መመስጠራቸዉ የሚያመለክት ነው።
  • ስካነር ይጠቀሙ: ማስፈንጠርያው ከመክፈትዎ በፊት የማስፈንጠርያውን ደህንነት ለመፈተሽ የሚያስችሉ ብዙ መሣሪያዎች (tools) መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ URLVoid, phishtank VirusTotal 
  • የፊደል አጻጻፍ እና የሰዋስው ስህተቶች ይመልከቱ ሊንኩ የያዘዉ መልእክት ብዙ ዜ የአፃፃፍ ስህተቶች ያሉባቸው ስለሆኑ መረጃ መንታፊዎች ወይም ከሌላ መረጃ ለመውሰድ የተላኩ መልእክቶች መሆናቸው የሚመላክቱ ጥሩ ምልክቶች ናቸው እንዲሁም ያልተለመዱ ወይም አዲስ ነገር ሲኖሩ መጠርጠር ይኖርቦታል። በዶሜይን ስሞች የተቀየረ ፊደል ከተመለከቱ አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ሊንኮች ምልክት መሆኑ ልብ ይበሉ።
  • ወቅታዊ የሆነ የደህንነት ዝመናዎች ያድርጉ - ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ መተግበርያዎች ወይም ፀረ-ቫይረሱን ማዘመን በአጥፊ ሶፍትዌሮች ሊደርስ የሚችል ጉዳት አነስተኛ የማድረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
  • ፀረ-አጥፊ ሶፍትዌሮች መጫን: ወደ ሚጠቀሙበት ስልክ አልያም ኮምፒዉተር የሚገቡ አጥፊ ሶፍትዌሮች ለመከላከልና አልያም የማንያ ወይም ማስጠቀቅያ ምልክቶች ያሳይዎት ይችላሉ

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር አጥፊ ተልእኮ ባላቸዉ አገናኞች(link) አማካኝነት ሊድርስብዎ የሚችለዉን የሳይበር ጥቃት ይከላከሉ።