የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

Nested Applications

Asset Publisher

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ Thu, 5 Jun 2025

ቋንቋዎቻችን በዲጂታሉ ዓለም ዳታ ውስጥ የሚቀመጡበትን ቴክኖሎጂ ማበልጸግ በዘመናችን የዲጂታል አብዮት ውስጥ የራሳችን ቦታ እንዲኖረን እንደሚያስችል ተገለጸ

ቋንቋዎቻችን በዲጂታሉ ዓለም ዳታ ውስጥ የሚቀመጡበትን ቴክኖሎጂ ማበልጸግ በዘመናችን የዲጂታል አብዮት ውስጥ የራሳችን ቦታ እንዲኖረን እንደሚያስችል ተገለጸ Thu, 5 Jun 2025

ማሕበራዊ ሚዲያን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ

ማሕበራዊ ሚዲያን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ Wed, 28 May 2025

የሳይበር ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ግንቦት 24 ይጠናቀቃል

የሳይበር ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ግንቦት 24 ይጠናቀቃል Wed, 28 May 2025

Asset Publisher

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር የተቀናጀ ዲጂታል የመሬት ምዝገባ እና ተያያዝ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የውል ስምምነቱ ከመሬት ምዝገባ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ዲጂታይዝ የማድረግ ሥራ፣ ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት (online services) የዲጂታል ክፍያ የካዳስተር ሥራ፣ የመሬት ምዝገባን ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር የማስተሳሰር፣ በከተማው ያለን የመሬት ሀብት መረጃ ሲስተም የመዘርጋት፣ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ፣ የመረጃውን ደህንነት የመጠበቅና ባለሞያዎች በራሳቸው መጠቀም እንዲችሉ ስልጠና የመስጠት ስራዎችን የያዘ ሲሆን  20 ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልጿል፡፡ 

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ደህንነቱ የተጠበቀ ስማርት ሲቲን እውን ለማድረግ የሚያስችል ሲስተም አበልጽጎ የሚያስረክብ ሲሆን ይህ ሲስተም ለአሥተዳደር ምቹ፣ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል፤ መንገድ፣ መብራት፣ ውኃ፣ የፖሊስ ሥራን የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያሳልጥ፤ ለዜጎች ምቹና ማራኪ የሆነ ኢንቨስትመንትን የሚጋብዝና ምርታማነትን የሚጨምር፤ ስማርት ከተማ መመስረት የሚያስችል ሲስተም ስንገነባ ይህ ሲስተም ደህንነቱ እንዲጠበቅ በዘላቂነት በትብብር እንሠራለን ብለዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቴክኖሎጂን ከማዘመን አኳያ የከተማው አስተዳደሮች ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ እንዲሆኑና ፕሮጀክቱን በየጊዜው በቅርበት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ / ተሾመ አዱኛ በበኩላቸው እንዳሉት ሸገር ከተማን የወደፊት  ስማርት ከተማ ለማድረግ የተያዘውን አላማ ለማሳካት የመሬት ምዝገባ /የካዳስተር/ ስራዎች ቁልፍ መሆናቸውን ገልጸው፤  ከዚህ ቀደም በከተማዋ የሚታየውን ያልተደራጃ እና  የተበጣጠሰ የመሬት አስተዳደር ስርአት ወጥ ወደ ሆነ  እና በቴክኖሎጂ በታገዘ  መልኩ በመስራት እና  ከተማውን የወደፊት ስማርት  ከተማ  ለማድረግ የያዝነው ራእይ ለማሳካት  እንደ ኢመደአ አይነት በዘርፉ እውቀት እና ልምድ  ካለው ተቋም ጋር መስራታችን ራእያችንን እውን ለማድረግ ያስችለናል  ብለዋል ፡፡