የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከኢ.ፌዲ.ሪ. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር የተቋሙን ድረ-ገጽ ፖርታል አበልጽጎ ለማስረከብ የሚያስችል የሥራ ውል ስምምነት (Web Portal Development Service Agreement) ተፈራረመ፡፡
በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የድረ-ገጽ ፖርታሉን ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ አበልጽጎ የሚያስረክብ ሲሆን በቀጣይ ሊጨመሩ ወይም ሊስተካከሉ የሚገቡ ነገሮች ካሉ በሁለቱ ተቋማት ተወካዮች አማከኝነት የሚከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢ.ፌዲ.ሪ. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የቀረበውን የመጀመሪያ ዙር ጅምር ድረ-ገጽ ፖርታል ስራ አድንቀው ከፖርታል ልማቱ በተጨማሪ የአገልግሎቱን ሠራተኞች ይሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ለማሳደግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ሰላማዊት አክለው እንደተናገሩት የሁለቱ ተቋማት ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡