የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጉብኝት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ የተመራ ሉካን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት በመገኘት ተቋሙ በቴክኖሎጂ ራስን ለመቻል እያደረገ ያለዉን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።

የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ተቋሙ የኢትዮጵያን የሳይበር ምህዳር ደህንነት ለማስጠበቅ እያደረገ ስላለዉ ስራ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ በኢመደአ በነበራቸዉ ቆይታ ተቋማቱ በትብብር መስራት በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረገዋል።

በይበልጥ ተቋማቱ በሳይበር ደህንነት እንዲሁም በመረጃና ኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች ልማት ላይ ተሞክሮዎችን ለመጋራትና የልምድ ልውውጥ  ለማድረግ  የሚከናወኑ ተግባራት  በላቀ ደረጃ እንደሚጠናከሩ መክረዋል።

በጉብኝቱ የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተገኙ ሲሆን በየሃገራቱ ያሉ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ትብብር በቀጥናዉ ላይ የሚስተዋለዉን አለመረጋገት ለመቀነስና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ጉልህ ሚና ይጫወታል

Asset Publisher