ኢመደአ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር የኮርት ሲስተምን ማዘመን የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መርብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር የኮርት ሲስተምን ማዘመን የሚስያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር ተፈራርሟል።

በመግባቢያ ስምምነቱ የተገኙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፍርድ ቤቶች የሚሰሩ ስራዎች ከሌሎች ተቋማት ጋር ከፍተኛ ትስስር ያላቸዉ በመሆኑ በቴክኖሎጂ ራሳቸዉን ማዘመን ከጊዜዉ ጋር አብሮ ለመጓዝ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ቀደም ብለን ስራዎችን በጋራ እየሰራን ቆይተናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ የዛሬዉ ስምምነት ሌላ ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል።

በጠቅላይ ፍርድቤቱ የሚተገበረዉ የዲጂታል ኮርት ሲስተም ከሁለት አመት ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ እዉን መሆን እንደሚገባዉ በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ ያነሱት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ጉዳዩን ቅድሚያ የምንሰጠዉ በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ ክትትልና ድጋፎች እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

በዉል ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸዉ የፍርድ ቤት ስራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቁ እንደሆነ በማንሳት እንደተቋም ያለንን አቅም ተጠቅመን የተሻለ የኮርት ስርዓት ለመተግበር ቁርጠኛ መኮኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ ፕሮጀክት የደህንነት ደረጃቸዉ ከፍተኛ የሆኑ የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች ከመተግበር ባሻገር እንደ ፒኬአይና ብሄራዊ መታወቂያን አቀናጅተን እንተገብራለን ብለዋል።

በኢመደአ የሚተገበሩ ሲስተሞች ከዚህ ቀደም በኢትዮ-ቴሌኮምና በአርተፍሻል ኢንተለጀንስ ሲስተሞች ጋር ተጣጣሚ በሆነ መልኩ የሚተገበሩ መሆኑን የጠቆሙት / ትዕግስት ሁሉም አካል ለፕሮጀክቱ ስኬት የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት የሚተገበረዉ ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ሰነዶችን ዲጂታል በማድረግ ግልፅ እና ተጠያቂነት ያለው የዳኝነት ስርዓት በመፍጠር ለፌዴራል ፍርድ ቤት እና ለክልል ፍርድ ቤት ቤቶች መሰረታዊ መፍትሄ ከመስጠቱም በላይ ፍርድ ቤቶችን የተቀላጠፈ እና ውጤታማ ስራዎችን እንዲያከናውኑ ከፍተኛ አስተዋፆ የሚያበረክቱ ናቸዉ።