"የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

"የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ የመካከለኛ ዘመን የግምገማ መድረክ /ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን (/) ጨምሮ የፌደራል እንዲሁም የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ወቅት ለዕቅዱ መነሾ የሆኑ ሀገራዊ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል። በኢትዮዽያ የሀገር በቀል ለውጥ አጀንዳ፣ ብሔራዊ 10 ዓመት ዕቅድ፣ የዘላቂ ልማት ግቦች ዕቅድ፣ የአፍሪካ ኅብረት አህጉራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ማዕቀፍ ውስጥ የመነጨው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በኢትዮጵያ ፈጠራ እና የእውቀት መሠረት ያለው ኢኮኖሚ ለማደርጀት ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂን እውን ለማድረግ እንደ ተቋም የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችና ስኬቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ ባቀረቡት ማብራሪያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መሰረት የሚሆኑ የዲጂታል ፕላትፎርሞችን (Digital Foundations) በማልማት እንዲሁም የሐገራችንን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የሰራቸው ስራዎች እና የተገኙ ስኬቶች ምን እንደሚመስሉ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ዋና የጀርባ አጥንት የሆነው ቁልፍ የሕዝብ መሰረተ ልማት የመረጃ ቋት ግንባታ (Public Key Infrastructure Data Center) መሆኑን የገለጹት / ትዕግስት ሃሚድ ይህንን እውን ከማድረግ አኳያ ኢመደአ የዚህን የመረጃ ቋት ግንባታ የማጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሌላው ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መሰረት የሆነውፋይዳየተሰኘው ብሔራዊ መታወቂያ ሲሆን ይህንን ፕሮግራም ከመደፍ አኳያ ኢመደአ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም / ትዕግስት አብራርተዋል፡፡ በሐገራችን የሚካሄደውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ከማዘመንና ደህንነት ከማረጋገጥ አኳያደራሽየተሰኘ ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ ፕላትፎርም በማልማት ተግባራዊ መደረጉን / ትዕግስት ገልጸዋል፡፡

በሌላም በኩል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ከማድረግ አኳያ የሐገራችንን የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ ቁልፍ አጀንዳ እንደሆነ የተናገሩት / ትዕግስት፤ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነትን እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በኩል ኢመደአ በርካታ የሕግ ማዕቀፎችን ማውጣቱን ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም፡ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ደህንነት ፍቃድና ቁጥጥር አዋጅ .. የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በሐገራችን የሳይበር ሥነ ምህዳር ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እና ከተከሰተም አፋጣኝ መፍትሄ ለመውሰድ የሚያስችልብሔራዊ የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከልበማቋቋም በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል ሥራ መሰራቱን / ትዕግስት አብራርተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ዝግጁነትና አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የሳይበር ደህንነት ፍተሻ በማድረግ ቀጣይነት ያለው የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ቁልፉ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ እንደሆነ የገለጹት / ትዕግስት፤ ከዚህ አኳያ ኢመደአ በራሱ አቅም በርካታ የሳይበር ደህንነት ቴክኖሎጂዎችን ማልማቱን ተናግረዋል፡፡ በኢመደአ የሚገኘውየኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕከልለዲጂታል 2025 አቅም የሚሆኑ ታዳጊ ወጣቶችን እያለማ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡