በሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ ህግና ስታንዳርድ ዙሪያ ለክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (Virtual Conference) ተካሄደ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ለሁሉም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም ለክልል የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሃላፊዎች በሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ ህግና ስታንዳርድ ዙሪያ የግንዛቤ መፍጠሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (Virtual Conference) በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ኮንፈረንሱን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ለመተግበር፣ በኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ፣ እንዲሁም ወጥነት ያላቸው የሳይበር ደህንነት ስታንደርዶችን ከመዘርጋት አንፃር የክልልና የከተማ አስተዳደር ሚናቸው የላቀ ነው ብለዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በአሁኑ ሰዓትም በዓለም ላይ ከሚስተዋለው የሳይበር ደህንነት ስጋትና ተጋላጭነት አንጻር ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለማወቅና ለመጠቀም፣ የህግ ማዕቀፎችና የቁጥጥር ስርዓቶች ለመዘርጋት፣ የጥናትና ምርምር አቅም ለመገንባት፣ ንቃተ ህሊናን ለማሳደግ፤ እንዲሁም ወቅታዊና ታሳቢ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ከግምት ያስገባ የፖሊሲ አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍ እና የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል መንግስት ደረጃ ኢመደአ የሳይበር ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመንደፍ፣ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ከመሰል ተቋማት ጋር አበረታች ስራዎች እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ሰለሞን ሶካ፤ በፌደራል ደረጃ የተጀመረውን የሳይበር ፖሊሲ ትግበራን እና የቁጥጥር ስርዓቶች ዝርጋታ ክልሎችም በሚያስተዳድሩት ክልል እና መዋቅር እንዲሁም ከተማ አስተዳደሮች ተጣጣሚ በሆነ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ በህግ አውጪው፣ ተርጓሚው እና አስፈፃሚ አካላት ዘንድ እስከ ታችኛው የክልሎቻቸው መዋቅር ድረስ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ ከሁሉም አካላት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል ፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች