ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንወጣለን፡ የኢመደአ አመራርና አባላት

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ የሦስት ሺ ዓመት ስልጣኔ ከባህር በር ጋር የተገናኘ እንደነበረና አሁንም ቢሆን የሕልውና መሠረት በመሆኑ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ የማይቀር መሆኑ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሊ ላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመችበትን አንደኛ ወር አስመልክቶ፤ “የባህር በር ባለቤትነት ለሀገራችን ሉዓላዊነት፣ ክብርና ብሔራዊ ጥቅም” በሚል መሪ ሃሳብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባዘጋጀው ወቅታዊ የውይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ክቡር አምባሳደር ፍስሃ ሻውል የኢትዮጵያ የዘመናት ታላቅ ስልጣኔ በቀይ ባህርም ሆነ በኤደን ባህረ ሰላጤ በኩል ከባህር በር ጋር የተቆራኘ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡

“አሁንም ቢሆን የባህር በር ጉዳይ የሕልውናችን መሰረት በመሆኑ ከሶማሊ ላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በተለያዩ አካላት ተቃዉሞ ቢገጥመውም ተግባራዊ መሆኑና በሰጥቶ መቀበል መርህ ፤ ኢትዮጵያም የባህር በር ባለቤት የመሆኗ ነገር የማይቀር መሆኑ በዉይይቱ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥዎችን ያሸነፈች ሀገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ እንዳታድግና እንደቀደመው ጊዜ ታላቅ እንዳትሆን እና የኢትዮጵያን እድገት ከማይሹ ሌሎችም ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚነሳ ጊዜያዊ ጫጫታና ተቃውሞ የማይቀርና የሚጠበቅም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም እውነታውን አውቆ የውስጥን አንድነት ማጠናከርና አንድ ላይ መቆም በእኛ በኩል የሚገባ መሆኑንም አምባሳደሩ አመላክተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት ሌላው የክብር እንግዳ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ እንደዚሁ የአምባሳደሩን ሀሳብ የሚያጠናክር ንግግር አድርገዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ስለኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ማንሳት የሚያሳፍርና አይነኬ የሚመስል ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት አቶ ጃፋር፤ “አሁን ግን በለውጡ መንግሥት ከዚህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ወጥተን በድፍረት የባህር በር ጉዳይን አንስተን ዋነኛ አጀንዳችን አድርገን እየሠራንበት በመሆናችን ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡

የማጠቃለያ ሃሳብ ያቀረቡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን ማደግ በማይፈልጉ ሀገራት ኢትዮጵያ እጅግ መሠረታዊ ከሆነው የባህር በር ተጠቃሚነት እንድትርቅ ተደርጋ መቆየቷን ገልጸዋል፡፡

“የአሁኑ ትውልድና መንግሥት ደግሞ ይህንኑ ተገንዝቦ የባህር በር ለማግኘትና የሀገራችንን የቀደመ ክብርና ታላቅነት ለመመለስ እየሠራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጅ ዕድገቷን የማይፈልጉት የቅኝ ገዥዎችን ሃሳብ የሚያራምዱ ሌሎችም ሀገራት መኖራቸው ሳያንስ ዛሬም ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር አብረው የሚሠሩ የውስጥ ባንዳዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ “የሀገርን ሉዓላዊነትና ጥቅም የማስከበር ትልቅ ኃላፊነት እንደተጣለበት ተቋም እንዲህ ዓይነቱን አስተሳሰብ የመዋጋትና የመመከት እጥፍ ድርብ ኃላፊነት አለብን” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ የማይቀር መሆኑን ያመላከቱት አቶ ሰለሞን፤ “ነገር ግን በዚህ ሂደት ደግፎና ተቃውሞ የቆመውን ሁሉንም ታሪክ ይመዘግበዋል፤ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆንን ግን ሀገራችንን ደግፈን፤ የተከፈለው ዋጋ ሁሉ ተከፍሎም ሀገራችንን የባህር በር ባለቤት ለማድረግ በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅብናል፡፡

ሀገራችን ታሪክ እየሠራች ነው ታሪክ እንሥራ፤ ለሚመጣው ትውልድም እንደቀደመው ዘመን ክብሯን የጠበቀች ታላቅ ሀገር እናሻግር” ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በማጠቃለያ መልዕክታቸዉ።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች