የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት / ሳሙኤል ክፍሌ የተመራ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ቡድን የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ቅጥር ግቢ ተገኝተው የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ጎበኙ፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር  አቶ ዳንኤል ጉታ ለዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን ኢመደአ ባለፉት አመታት የሃገሪቱን የሳይበር ደህንነት በመጠበቅ የሰራቸውን ስራዎች እና በምርምር እና ልማት የታጠቃቸውን ምርት እና አገልግሎት አስጎብኝተዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በመጠበቅ እንዲሁም ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ለሃገራዊ ሰላም፣ ልማት እና ዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ እንደሆነ አቶ ዳንኤል ጉታ ለዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች አብራርተዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  የሐገሪቱን የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ በኩል በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሃይል እና በአሰራር ሥርአት ረገድ የደረሰበት ደረጃ ጠቃሚ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በተለይም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጣኦ ያላቸውን ታዳጊዎች ለመኮትኮት የሚያስችል የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በማደራጀት እና በሳይበሩ ዘርፍ የነገ ሃገር ተረካቢ ታዳጊ እንዲሆኑ እየሰራ ያለው ሥራ አበረታች ነው ብለዋል::

በቀጣይም የኢመደአን ልምድ በመውሰድ  በቴክኖሎጂ እና በተለያዩ የምርምር ስራዎች ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች