ለግል የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ፣ አለምአቀፍ አጋር ያላችሁና በሃገር ውስጥ ለሚሰሩ ቴክኖሎጂ ተቋማት እና ስታርትአፖች የተላለፈ ጥሪ
ለግል የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ፣ አለምአቀፍ አጋር ያላችሁና በሃገር ውስጥ ለሚሰሩ ቴክኖሎጂ ተቋማት እና ስታርትአፖች የተላለፈ ጥሪ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በየዓመቱ ጥቅምት ወር የተለያዩ አለምአቀፍና ሃገር አቀፍ ተቋማት በተገኙበት የሳይበር ደህንነት ወርን ያከብራል:: በመሆኑም ዘንድሮም በ2016 ዓ.ም በአለምአቀፍ ደረጃ “Secure Our World” በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ጊዜ እንዲሁም በሃገር አቀፍ ደረጃ “አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሃገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል ለሚያከብረው 4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የግል ቴክኖሎጂ ተቋማት ፣ አለምአቀፍ አጋር ያላችሁና በሃገር ውስጥ ለሚሰሩ ቴክኖሎጂ ተቋማት እና ስታርትአፖች ምርትና አገልግሎታቸዉን ከጥቅምት 12-15/2016 ዓ.ም በግዮን ሆቴል በሚካሄደው አዉደ-ርዕይ መርሃ-ግብር ላይ እንዲያስተዋዉቁ ከወዲሁ ለመጋበዝ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም፡-
• ማቅረብ የሚፈልጉት የቴክኖሎጂ ምርት እና አገልግሎት የሚገልጽ ጽሁፍ
• የድርጅቱን ፕሮፋይል የያዘ ሰነድ
• ለእይታ የሚቀርብ የቴክኖሎጂ ዉጤት ማቅረብ የምትችሉ ተቋማት ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎችንና ማስረጃዎችን እንዲሁም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ጎግል ፎርም በመሙላት contact@insa.gov.et በኢሜል አድራሻ ላይ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳስቢያ፡- በሳይበር ደህንነት ምርትና አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
ጎግል ፎርም ሊንክ: https://docs.google.com/.../1FAIpQLScixToIdL4.../viewform...
“አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሃገር ሉዓላዊነት”
Resilient Cyber Security Capability for National Sovereignty