የኢመደአ አመራር እና አባላት ለ32ኛ ጊዜ የደም ልገሳ አደረጉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

”አንድም እናት በደም እጦት መሞት የለባትም“ በሚል መሪ ቃል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራር እና አባላት ለ32ኛ ጊዜ የደም ልገሳ አደረጉ፡፡

በልገሳው መርሃ ግብር የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ አመራር እና አባላት የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡

ኢመደአ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር በየ3 ወሩ የደም ልገሳ ፕሮግራም በማዘጋጀት በተቋሙ የደም ልገሳ ባህል እንዲሆን በማድረጉ እና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣቱ ከብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል፡፡