ሐገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ደረጃ ጥናት ውጤት

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የተሰራው “ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ ጥናት” በሐገር አቀፍ ደረጃ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ወጥ በሆነ መልኩ የተሰራ የመጀመሪያ ጥናት ነው፡፡

ጥናቱ በዋናነት በኢትዮጵያ የሳይበር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ዜጎች ስለ ሳይበር ደህንነት ያላቸው የእውቀት (Knowledge) ፣ የአመለካከት (Attitude) እና የአጠቃቀም (Practice) ደረጃ ምን ይመስላል በሚል ጭብጥ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

የጥናቱ ፓፑሌሽን የዳሰሰው በሀገሪቱ የሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጎች ሲሆን፤ የጥናቱ ናሙና ቁጥር በፕሮባቢሊቲ ሳምፕሊንግ ዘዴ የተመረጡ ከ33.9 ሚሊየን ውስጥ 6458 ዜጎች ለማሙና ተመርጠዋል፡፡ በዚህም 6106 መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡

የጥናቱ ናሙና አመራረጥ ደረጃዎች በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ክልሎችና ሁለት የከተማ መስተዳድሮች ተመርጠዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የየክልሎቹ ዋና ዋና ከተሞችና ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ተጨማሪ ከተሞችም ተመርጠዋል፡፡

የጥናቱ ተሳታፊዎች የእድሜ ክልል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት እና 51% የሚሆኑት ከ 14- 25 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ 36.4% የሚሆኑት እና በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚሆኑት ደግሞ ከ25-35 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኛቸው ፡፡

የጥናቱ ተሳታፊዎች የትምርት ደረጃ በተመለከተ 41.7 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፣ 26.4% የሚሆኑት ዲፕሎማ፣ 18.6% የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ፣ 8.1 % ማስተርስ፣ 3.7 % የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ፣ 1.1% ፒ.ኤች.ዲ እና 0.3% ሌላ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ናቸው፡፡

የጥናቱ ጠቅላላ ውጤት እንደሚያሳየው 65 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ እንዳላቸው ተነው፡፡

አጠቃላይ የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ስታትስቲክስ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

• አማካይ አጠቃላይ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና እውቀት ደረጃ፤ 29.23% እውቀት የሌላቸው፣ 35.60% ዝቅተኛ እውቀት፣ 11.75% መካከለኛ እውቀት፣ 23.40% ከፍተኛ እውቀት፤

• የሳይበር ደህንነት የአመለካከት ምዘና ውጤት፤ 47% አጠቃላይ አወንታዊ አመለካከት፣ 53% አጠቃላይ አሉታዊ አመለካከት፤

• አጠቃላይ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ልምምድ ውጤት፤ 50.2% አዎንታዊ ልምምድ፣ 49።8% አሉታዊ ልምምድ፤

• የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ያላቸው ኢትዮጵያዊያን፤ 35% እውቀት ያላቸው፣ 65% እውቀት የሌላቸው፤

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች