የአመራር ልሕቀት በሳይበር ዘመን” በሚል ርዕስ አገራዊ ሴሚናር ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]
አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 29/2015 ዓ/ም፡ “የአመራር ልሕቀት በሳይበር ዘመን” በሚል ርዕስ ሴክተር-አቀፍ አገራዊ የአመራር ሴሚናር በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አዘጋጅነት ተካሄደ፡፡
በሴሚናሩ ላይ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም የግል ድርጅት መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሴሚናሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት የሴሚናሩ ዋና ዓላማ የየሴክተሩን በጎ የአመራር ተሞክሮዎች በማስፋት፣ የተናበበ የጋራ የአመራር እሴት በመፍጠር በአገር ግንባታ ሂደት የአገር-በቀል የአመራር ጥበብን ማጎልበት ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪም በየሴክተሩ በጥናት የተለዩ፤ ውጤት ያስገኙ አገር-በቀል የአመራር አስተሳሰቦችን እና ድርጊቶችን እንዲሁም አርአያ የሆኑ በአገራችን የሚገኙ የተለያዩ ሴክተሮች አመራሮችን ተሞክሮዎች በመቀመር ለመማማሪያነት መጠቀም፤ በሳይበር ዘመን ቁልፍ የአመራር ክህሎቶች ምን እንደሆኑ የልምድ ልውውጥ ማድረግና ለአገር አቀፍ የአመራር ፍላጎት ግብአት የሚሆኑ ሃሳቦችን ማመንጨት እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይህንን ሴክተር-አቀፍ አገራዊ የአመራር ሴሚናር ሲያዘጋጅ በዋናነት በሕዝብና በመንግስት የተሰጠውን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮ ባሻገር የሳይበር ምህዳር ልዩ ባህሪያትን ጠንቅቀው የሚረዱና በየሴክተሩ ወደፊት ሊያሻግሩ የሚችሉ መሪዎችን ለመፍጠር መነሻ መድረክ እንደሚሆን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አቶ ሰለሞን ሶካ አብራርተዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በሴሚናሩ ላይ “የሳይበር ደህንነት” በሚል ርዕስ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፤ በገለጻቸውም የሳይበር ምህዳር አለማችንን እየመራ የሚገኝ አዲስ አውድ መሆኑን ገልጸው በዚህ አውድ ላይ የመሪዎች ሚናና ልህቀት ምን መምስል እንዳለበት አብራርተዋል፡፡
ሌላው በሴሚናሩ ላይ ተገኝተው ገለጻ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ሲሆኑ “ተቋማዊ ልሕቀት” በሚል ርዕስ ተቋማትን እንዴት መገንባት እንደሚቻል ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም በኢትዮጵያ የተቋማት ግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ማነቆዎችን እና የመፍትሄ ሃሳቦችን አብራርተዋል፡፡
በተመሳሳይ በሴሚናሩ ላይ በመገኘት “የአመራር ልሕቀት” በሚል ርዕስ ገለጻ ያቀረቡት አቶ ለማ ደገፋ በበኩላቸው፤ አመራር ምን እንደሆነ፣ የውጤታማ አመራር ባህሪያትን እንዲሁም በሳይበር ዘመን የአመራር ልሕቀት ምን እንደሚመስል አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም በሴሚናሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮች የተለያዩ ጥያቄዎችንና ሃሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን፤ በኢመደአ አዘጋጅነት የተካሄደው “የአመራር ልሕቀት በሳይበር ዘመን” ሴክተር-አቀፍ አገራዊ የአመራር ሴሚናር ወቅቱን የዋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን ገልጸው እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ መድረኮች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ለዚህም የሚመለከተው ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
በሴሚናሩ ማጠቃለያ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት “ሁላችንም ተናበን በጋራ መስራት ካልቻልን ሃገር መገንባት አንችልም” ያሉ ሲሆን እንደ ሃገር ምርጥ የአመራር ተሞክሮዎችን ለማጋራት የሚያስችል የውይይት መድረክና ሴሜናር በታቀደ መልኩ በቀጣይነት ሊዘጋጅ ይገባል ብለዋል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
 
ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች