ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከጥር 30/2016 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒ ኤች ዲ) ተሾመዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኔትወርክ ኢንጂነር ባለሙያነት ጀምሮ እስከ ዲቪዥን ሃላፊነት ለ14 አመታት ያክል ተቋሙን አገልግለዋል፡፡ በ2014 ዓ/ም ተቋሙን ከለቀቁ በኋላም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚኒስትር ቴክኖሎጂ አማካሪ ሆነው ለአንድ አመት ሰርተዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ኢመደአ በመመለስ ከነሃሴ 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፤ ከጥር 30/2016 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒ ኤች ዲ) ተሾመዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን የማስተርስ ዲግሪያቸው ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ሮበርት ጎርደን ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን እና ኔትወርክ ሴኪዩሪቲ አግኝተዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራርና አባላትም ለወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ መልካም የሥራ ጊዜን ይመኛሉ፡፡