በኢትዮጵያ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ መሆናቸው ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 22/2014: ባለፉት ሦስት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ እንደገለጹት 122 ሺህ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ከእነዚህ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አቶ አሸናፊ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የህውሐት አሸባሪ ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17 ሺ የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ የጥፋት ቡድን ተከፍተው ነበር ብለዋል፡፡

በአሸባሪዉ ቡድን በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች በአንድ ቀን ብቻ 25ሺ የሚደርሱ መልዕክቶች በቲውተር ምህዳሩ ላይ ይሰራጩ እንደነበርም ነው ሃላፊዉ የገለጹት፡፡

የጥፋት ቡድኑ እነዚህን ሁሉ ዘመቻዎች አድርጎ አልሳካ ሲለው ለሽብር ትግባር ተባባሪ ከሆኑ ሃገራት እገዛ በማግኘት እንዲሁም አስቀድመው አስርገዉ ያስገቧቸዉን ሰዎች በመጠቀም ከእውነታ ውጪ የሆኑ ዘገባዎችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ተዋቂዎቹ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችም ከጥፋት ቡድኑ ጋር የተያያዙ ወይም ለቡድኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ይዘቶች በፕላትፎርማቸው ላይ እንዲኖሩ ወይም እንዲቆዩ ከመፍቀድ ባለፈ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆኑ ለሌሎች አካላት በስፋት ያሰራጩላቸው /Suggest/ ያደርጉላቸው እንደነበረም አቶ አሸናፊ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀገርን አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ አካውንቶችን የመዝጋትና መረጃዎቻቸው እንዳይሰራጩ የማድረግ እንዲሁም አንዳንድ አካውንቶችን መረጃ እንዳይለጥፉ ከማድረግም ባለፈ ለተለያየ ጊዜ ሲዘጓቸው እንደነበር አቶ አሸናፊ አብራርተዋል፡፡

እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሚያሳዩት በጦር መሣሪያ ከሚደረገው ጦርነት በተጨማሪ በመረጃ ጦርነቱ መስክ አስቀድሞ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ አሽባሪዉ ቡድን ጉልበት ያለዉ በማስመሰል ከፍተኛ የሆን የፕሮፖጋንዳ ስራ ሲሰራባቸው እንደነበረ የሚያመለክቱ መሆናቸውን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች