ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሀገራችን አሁን እያከናወነችዉ ካለችው የህግ ማስከበርና የህልዉና ዘመቻ ጋር እንዲሁም ሌሎች ቀጠናዊና አለምአቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ጠላቶች እና ተባባሪዎቻቸው ከውስጥና ከውጭ ሆነው የሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም በተለያዩ የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮች ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ለመፈጸም ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡

ነገር ግን አሁን እየታዩ ያሉት አዝማሚያዎችና ሙከራዎቻቸውን ማሳሰብና ማሳውቅ አስፈልጓል፡፡ እነዚህ እኩይ ዓላማ ያላቸው አካላት እዚሁ ሀገር ዉስጥ ሆነው የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮችን እንዲሁም ሲስተሞችን እንዲያስተዳደሩ በተቋማት መብት የተሰጣቸውን (System Admins) ነገር ግን ለሙያቸው፤ ለተቋማቸውና ለሀገራቸው ታማኝ ያልሆኑ ጥቂት ጡት ነካሽ ባንዳዎችን በመጠቀም እክል ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ማንኛዉንም የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮችን እንዲሁም ሲስተሞችን የምታስተዳደሩ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ሲስተሞችን እንዲያስተዳደሩ መብት የተሰጣቸው ወይም የተቋማትን የሶሻል ሚዲያ አካውንቶችን እንዲያስተዳድሩ የይለፍ-ቃል ወይም Password እንዲይዙ የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ወይም (System or Netwok Admins) ትክክለኛውን የሙያ ብቃት እና ጥብቅ የስነ-ምግባር ማጣራት የተደረገባቸው መሆኑን ደግማችሁ፣ ደጋግማችሁ እንድታረጋግጡ እናሳስባለን፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

መስከረም 28/2014

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች