የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ የካቲት 2/2014: የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ከቱምሳ ዴሎፕመንት ግሩፕ ጋር በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የሳይበር ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ኤጀንሲዉ በሃገሪቱ ያሉ ወሳኝ የኢንፎርሜሽን እና የመገናኛ መሰረተ-ልማት ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ  ከፍተኛ አቅም  እየፈጠረ መምጣቱን ጠቁመዉ የቱምሳ ዴቨሎፕመንት ግሩፕ ራሱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በያዘዉ እቅድ ኢመደኤን በመምረጣቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

 

 

 

ኢመደኤም የቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ ከሚያደርገዉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ድጋፍ ጎን ለጎን የኮምፒዉተር እና የኮምፒዉተር መሰረተ ልማቶች ደህንነታቸዉን  ለማረጋጥም ከፍተኛ ስራዎችን ይሰራል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ኩባንያዉ በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ራሱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚስራቸዉ ስራዎች ሁሉ ኢመደኤ ከጎኑ ይሆናል ብለዋል።

 

የቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ በመወከል በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሽፈራዉ ጃርሶ አሁን ላይ የዲቭሎፕመንት ግሩፑ ከፍተኛ የሚባሉ እና ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸዉን ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም በቴክኖሎጂ ስራዎቹ ባለመደገፋቸዉ ማግኘት ያለበትን ጥቅም አላገኘም ብለዋል።

በመሆኑም ይህን የመግባቢያ ስምምነት የፈረምነዉ በተቋማችን ያለዉን ተለምዶአዊ አሰራር በማዘመን ረገድ ኢመደኤ የቴክኖሎጂ ክፍተታችንን በመሙላት የተሻለ ስራ ለመስራት ያግዘናል ብለን በማመናችን ነው ብለዋል።

የቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ በተለያዩ የህዝብ አገልግሎት ዘርፍ መሰማራቱን ያወሱት አምባሳደር ሽፈራዉ ከእነዚህ ዘርፎች መካከልም የትራንስፖርት ፣ የግብርና እና የማእድን ዘርፍ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ መሆናቸዉን ጠቁመዋል።  

 

በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሰረትም ኢመደኤ የቱምሳ ዴቭሎፕመንት ግሩፕ ራሱን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ሂደት ዉስጥ ከእቅድ ጀምሮ በቴክኖሎጂ ልማት እና የማማከር ስራ የሚሰራ ሲሆን ለእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ የተለያዩ የሳይበር ደህንነት መፍትሄዎች የሚያቀርብ ይሆናል።