የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከቀደሙት ጊዜያት በተሻለ በዚህ አመት የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ማደጉን ገልጸ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

 

አዲስ አበባ የካቲት 7/2014: የኤጀንሲዉን የስድስት ወር የእቅድ ክንውን አፈጻጸም አስመልክቶ በዛሬዉ ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛዉ በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የመጀመሪያዉ በሀገራችን እያደገ ሰለመጣዉ የሳይበር ጥቃት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ግማሽ አመት ብቻ 3400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች በሀገሪቱ መፈጸማቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የዘንድሮው የሳይበር ጥቃትም በሀገሪቱ የሳይበር ጥቃት ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አውስተው ለጥቃቱ ማደግም ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጠናዊ እና ሀገራዊ ምክንያቶች አሉት ብለዋል።

ኤጀንሲዉ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ የሚባል ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት / ሹመቴ ሆኖም በግለሰቦች፣ በተቋማት እና በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የአጠቃቀም ክፍተቶች ለጥቃቱ ማደግ የጎላ ድርሻ እንደነበራቸው ተናግረዋል ።

 

የጥቃት ሙከራዉ ካለፈው 2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በዚህ በጀት አመት የተሞከረዉ የሳይበር ጥቃት መጠን በሶስት እጥፍ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም የጥቃቱ መጠን ከአመት  አመት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደመጣ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አብዛኛቹ ጥቃቶችም ትኩረታቸዉን በፋይናንስና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ማድረጋቸዉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የክልል ቢሮዎች፣ የት/ ተቋማት፣ ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች እና ሚዲያ ተቋማት ዋነኛ የጥቃት ዒላማዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

በሁለተኛ ደረጃ በሃገሪቱ ባለፉት ስድስት ወራት ስለተከሰቱ የጥቃት አይነቶች እና ኢላማዎች ማብራሪያ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ በስፋት የተሞከሩት የሳይበር ጥቃት አይነቶች መካከል የመሰረተ-ልማት ቅኝት (33 በመቶ) የሚሆነዉን ከፍተኛ የጥቃት መጠን የያዘ ሲሆን የድረ-ገጽ ጥቃት እና የማልዌር ጥቃቶች እንደየቅደም ተከተላቸዉ ከፍተኛ የጥቃት ሙከራ የተደረገባቸዉ እንደነበሩ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ ጥቃቶች መካከልም ከጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኛዎቹን ጥቃቶች ኢመደኤ ማክሸፍን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ጥቃቶቹ ቢደርሱ ኖሮ በግለሰብ፣ በተቋማት እና በሀገር ደረጃ ሊያደርሱ የሚችሉት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ክስረት በጣም ከፍተኛ ይሆን እንደነበረም አብራርተዋል፡፡

ሆኖም በዚህ አመት ኤጀንሲዉ ከባለፉት አመታት የበለጡ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ቢቃጡም ራሱን ከሁኔታዎች ጋር ቶሎ በማላመድ እና በመራመድ የመከላከል አቅሙን 96 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

ከዋልታ ሚዲያ የፌስቡክ ገጽ መጠለፍ ጋር በተያያዘም ለአካውንቱ መጠለፍ ሁለት ምክንያቶችን ዋና ዳይሬክተሩ ያነሱ ሲሆን የመጀመሪያው ምክንያትም የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ካሉት 4 ዋና አድሚኖች ውስጥ 3 በኢትዮጵያ ያሉ ሲሆን አንደኛው አካል ግን በአሜሪካን እንደሚገኝ ለማወቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት አክሰስ እንዲያደርጉ ሃላፊነት ከተሰጣቸው ሠራተኞች አንዱ በግል የተላከለትን አጥፊ ተልዕኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ተናግረዋል።

መረጃ መንታፊዎች የተቋሙን የፌስቡክ ገጹን ለመጥለፍ "ራንሰምዌር" የመረጃ ጥቃት ማደረሻ ስልትን የተጠቀሙ ሲሆን የፌስቡክ አካዉንታቸዉን መልሶ ለማግኘት ወይም ለማስለቀቅ የራንሰም ክፍያን እንዲፈጸምላቸዉ እንደጠየቁ ተገልጿል።

በምህዳሩ እያደገ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ህጎችን መመሪያዎችን እና ፕሮሲጀሮችን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ አገልግሎት ሰጪዎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን ሚዲያዎች የራሳቸዉን ተቋም ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ ያላቸዉን ተደራሽነት በመጠቀም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማሳደግ ስራ መስራት ይገባቸዋልም ሲሉ አጽንዎት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ዋና ዳይሬክትሩ የሳይበር ጥቃት መከላከል ላይ ሊሰሩ ስለሚገቡ ጉዳዮች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን እንደ ሃገር ኢመደኤ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉአላዊነት ለማረጋገጥ የሚሰራዉ ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን የሳይበር ምህዳሩን ደህንነት የማረጋገጥ ድርሻውን አጠናሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

"የሳይበር ደህንነት የሁሉም ኃላፊነት ነው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ተቋማት ስነ-ምግባር የተላበሱ ሙያተኞችን እንዲኖራቸው በመሥራት፣ የሳይበር ደህንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ፣ የሚጠቀሙባቸውን ሲስተሞች ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ኦዲት በማስደረግ እና የአሠራር ሥርዓቶችን በአግባቡ በመተግበር የሳይበር ደህንነትን ሊያረጋግጡ ይገባል ሲሉ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ለጋዜጠኖች በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል፡፡