በበይነመረብ የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችን እና ጥቃቶችን መከላከል ላይ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ መጋቢት 27/2014: በበይነ-መረብ የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችን እና ጥቃቶችን መከላከል የሁሉም ሃላፊነት መሆኑ ተገለጿል።

“ሁሉን አቀፍ እና አካታች የዲጂታል ሽግግር” በሚል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት በተካሄደዉ ኮንፈረንስ መዝጊያ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ም/ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሶሎሞን ሶካ እንዳሉት በበይነ-መረብ የአጠቃቀም ክፍተቶችን እና የግንዛቤ እጥረት ሳቢያ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀዉሶች እየጨመሩ መጥተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከበይነመረብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀዉሶችን ግምት ዉስጥ ያስገባ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በዚህ ሂደትም ከአጠቃቀም ክፍተት ጋር በተያያዘ ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ትንኮሳዎችን መለየት እና መከላከል በሚያስችሉ መልኩ በዲጂታል ሚዲያዉ፣ በሳምንታዊ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ፕሮግራም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እና የገጽ ለገጽ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በኦንላይን የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና ትንኮሳዎችን መከላከል ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሰይሆን የሁሉም ሃላፊነት ነው ያሉት ሃላፊዉ በይበልጥ ደግሞ ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጀት መስራት በታዳጊዎች ላይ ለሚሰራው የተቀናጀ ስራ ወሳኝ ድርሻ እንዳለዉ ገልጸዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ ለትንኮሳ ተጋላጭ ለሆኑት ሴት ተማሪዎች የግንዛቤ መስጨበጫ ስራ መስራቱ ለሌሎች የትምህርት ተቋማት እንደምሳሌ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል መሆኑን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጥናት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ቢኒያም ቻኪሉ በበኩላቸዉ በበይነ-መረብ አማካኝነት በሴቶች ላይ የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን እና መሰል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ ዩኒቨርሲቲዉ የግንዛቤ መስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በስልጠናዉ ከ 3600 ሴት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ማሳተፋቸዉን የገለጹት ዶ/ር ቢኒያም በአማራ ክልል ባሉ 13 ዞኖች 45 ት/ ቤቶችን 90 የሚሆኑ የአይሲቲ መምህራንን ማሳተፋቸውን ጠቁመዋል።

“ሁሉን አቀፍ እና አካታች የዲጂታል ሽግግር” በሚል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ኮንፈረንስ ተጠናቋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች