ኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕከል ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ የሚሆን ነው - ክቡር ሼክ መንሱር ቢን ሙሳላም

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ተቋም (Organization for Educational Cooperation - OEC) ዋና ጸሃፊ ሼክ መንሱር ቢን ሙሳላም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና /ቤትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን ሀገር በቀል የሳይበር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች የማልማት ሥራን ጎብኝተዋል። ስራዎቹና ተሞክሮቹ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

ሼክ መንሱር ቢን ሙሳላም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው ትምህርትን በማቅረብ፣ በሳይበር ሉአላዊነት፣ በዲጂታላይዜሽን እና በታለንት ልማት ዙሪያ በአፍሪካ ደረጃ እየተሰራ ያለውን ሥራ ለመመልከት የሚያስችላቸውን ጉብኝት አካሂደዋል፡፡ አፍሪካውያን በዜጎቻቸው የሚለሙ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ በመጠቀም የዲጂታል ሉዓላዊነታቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል ያሉት ሼክ መንሱር፤ ከዚህ አኳያ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የለሙና እየለሙ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ ለአህጉሩም ጭምር ተስፋ ሰጪ ናቸው ብለዋል፡፡

ኢመደአ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በማልማት ረገድ የጀመረው ሥራ ከሳይበር ደህንነት ውጪ በሌሎች ዘርፎች ላይም ለተሰማሩ ተቋማት ምሳሌ እንደሚሆን የገለጹት ሼክ መንሱር፤ በሁሉም ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች እንዳሉና እነዚህን ማልማት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ተቋም (Organization for Educational Cooperation - OEC) .. 2020 የተቋቋመ ሲሆን ዋና ዓላማውም በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በካሪቢያን ያሉ የተቋሙን አባል አገራት የልሂቃን፣ የሃብት እና መሰል አቅሞችን በማስተባበር  ጥራት ያለውና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አካታች ትምህርት ለሁሉም በማቅረብ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው፡፡

ዋና ጸሃፊ ሼክ መንሱር ቢን ሙሳላም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና /ቤትን ከመጎብኘታቸውም በተጨማሪ ክቡር ምክትል /ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ማነጋገራቸውም ይታወቃል።