ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወ/ሮ አስቴር ዳዊትን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል፡፡

ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆኑ ሲያገለጉ የነበሩ ሲሆን፤ የሥራ ልምዳቸውን የጀመሩት በወላይታ ዞን ጤና መምሪያ በኤች አይ ቪ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ በመሆን ነው፡፡ በመቀጠልም በሶዶ ከተማ የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ፣ በወላይታ ዞን የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ እንዲሁም የወላይታ ዞን የገጠር ዘርፍ ሃላፊ፣ በአፍሪካ ሊደርሺፕ አካዳሚ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር እንዲሁም የምርምር ዳይሬክተር፣ በኢፌዲሪ የሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ በመሆን አገልግለዋል፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የተቀናጀ ድጋፍ ክንፍ ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ ለሌላ ሃላፊነት ወደ ሌላ ተቋም መሄዳቸው ይታወሳል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራር እና አባላትም ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በኢመደአ በሚኖራቸው ቆይታ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ፡፡