ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ1443ኛው የኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ - ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እና ለተቋሙ የእስልምና እምነት ተከታይ አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ ይህንን በዓል ሲያከብር በእዉነተኛዉና በተለመደው የኢትዮጵያዊ ባህላችን የሌላውን ወገናችንን ደህንነት በማሰቀደምና በታላቅነት እሳቤ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

“ሕዝበ ሙስሊሙና ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የታላቅነትን ሚስጥር እንያዝ። በታላቅነት እንኑር። ታላቅነት ከተወለድንበት ዘር፤ ከመጣንበት አቅጣጫ፤ በምንጠራበት ስም እና ከምንከተለው ሃይማኖት አይጀምርም፡፡ የታላቅነት መጀመሪያዉና መገለጫው ለሌሎች ከማሰብና ለሌሎችም ከመኖር ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የእስልምና ሀይማኖት የተቸገሩትን በመርዳት የሚታወቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በችግር ላይ የሚገኙትን ወገኖች ዘር፣ ሀይማኖት፤ ጾታ፤ ቦታና ሁኔታ ሳይለይ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያዊነትም መገለጫው መረዳዳትና አብሮ ማዕድ መቁረስ፤ ሀዘንን መጋራት፤ የጎደለውን መሙላት፤ ክፋትን መኮነን፤ አጥፊዎችን መምከርና መመለስ በመሆኑ ይህንን አብሮ የቆየ ባህላችንን ታሳቢ በማድረግ ዕለቱን እንድንዘክር በማስታወስ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡