ኢመደአ ተመራቂ ኤፍሬም በለጠና እናቱን ወ/ሮ ተዋበች ኮሻን ለማገዝ ቃል ገባ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ11 ቀን 2014 ዓ/ም : የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እና የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተሮች የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራቂ የሆነው ኤፍሬም በለጠ እና እናቱን ወ/ሮ ተዋበች ኮሻን በኢመደአ ዋና መስሪያ ቤት አቀባበል አድርገውላቸዋል::

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ተመራቂ ኤፍሬም በለጠን እና እናቱ ወ/ሮ ተዋበች ኮሻን በተቀበሉበት ጊዜ እንዳሉት የብዙ የኢትዮጵያን እናቶችን ድካም እና ልፋት በሚያሳይ መልኩ እናትህን በማመስገንህ እና ለዚህ በመብቃትህ እንኳን ደስ ያለህ ብለውታል፡፡ አያይዘውም ኢመደአ እንደ ህዝባዊ ተቋም ለብዙ ወጣቶች ምሳሌ የሆነውን ተመራቂ ኤፍሬም በለጠን በልዩ ሁኔታ ቀጠሮ ከማሰራት ጀምሮ በሌላ በማንኛዉም ተቋሙ በሚችለው ሁሉ ለማገዝ እንዲሁም ቤተሰቡን በተለይ ደግሞ የብዙ ኢትዮጵያዉያንን እናቶች የምትወክለውን እናቱን ወ/ሮ ተዋበች ኮሻን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል::

ተመራቂ ኤፍሬም በለጠ እና ወ/ሮ ተዋበች ኮሻ በበኩላቸው ኢመደአ ላደረገላቸው መልካም አቀባበል እና ለተበረከቱላቸው ስጦታዎች ሁሉ ተቋሙን አመስግነው፤ በታማኝነት ሃገርን የሚያገለግል፤ አክባሪና ተዘካሪ በሆነ ተቋም በመገኘታችን ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል::

በተጨማሪም ተመራቂ ኤፍሬም በለጠ በኢመደአ የኢትዮ_ሳይበር ታለንት ልማት ማእከል በመገኘት በማዕከሉ ውስጥ እየሰለጠኑ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ባስተላለፈው መለክት እናታችሁን፤ ሃገራችሁንና ሙያችሁን ውድዱ ብሎ አደራውን አስተላልፏል፡፡ ልምዱንም አካፍሏል፡፡