ኢትዮጵያ የራሷን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በመገንባት የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል እየሰራች ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]


 ኢትዮጵያ የራሷን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በመገንባት የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል እየሰራች መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ሹመቴ ግዛው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ማደግ ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እያደጉ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያም የሳይበር ጥቃት ሙከራ እየጨመረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ የሰለጠነ እና በሙያ ስነ-ምግባሩ የታነፀ የሰው ኃይል በማፍራትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን በራስ አቅም በማጎልበት የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል እየተሰራ ስለመሆኑ አክለዋል፡፡

በተለይ በራስ አቅም ዲጂታል መተግበሪያዎችን ማጎልበት የቴክኖሎጂ ባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል አቅም እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በየደረጃው ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ ላስቀመጠቻቸው እቅዶች ስኬት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ ዋነኛው መሆኑንም አንስተዋል።

ከዚህ አኳያ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከዋሉት የሳይበር ጥቃት መከላከያና መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት በሀገር ውስጥ አቅም የተዘጋጁ ናቸው።

በቀጣይም ይህንን ጥረት በማሳደግ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ በራሷ አቅም በለሙ ቴክኖሎጂዎች የሳይበር መከላከል ሥራዎችን እንደምታከናውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቀጣናውን ጂኦ-ፖለቲካ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል እየሰራች ስለመሆኑም ነው ያብራሩት፡፡

በአሁኑ ወቅት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የሳይበር ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም እንዲሁ።