ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ማዕከል ያደረጉ 9 ሺ የሚጠጉ የሳይበር ጥቃቶች በኢትዮጵያ ላይ ተሞክረዋል - አቶ ሰለሞን ሶካ፡ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ማዕከል ያደረጉ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ የሳይበር ጥቃቶች በኢትዮጵያ ላይ መሞከራቸውን እና ከዚህም ውስጥ 97 በመቶ የሚሆኑትን ማክሸፍ መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢመደአ 2014 በጀት አመት ከተቃጡ 8 985 የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ 45 ከመቶ የሚሆኑት ቁልፍ የሀገሪቱን መሰረተ ልማት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውም ጠቅሰዋል።

 የጥቃት ሙከራዎች ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል የፋይናንስ ተቋማት፤ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች፣ ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ የመንግስት የፖለቲካ አደረጃጀቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የጤና ተቋማትና የግል ድርጅቶችም ይገኙበታል ብለዋል  ፡፡

ኢመ በበጀት ዓመቱ 99 ተቋማት ላይ  የሳይበር ደህንነት ፍተሻ እና ግምገማ (የሳይበር  ደህንነት ኦዲት) ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም ተቋማት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉባቸውን በርካታ ክፍተቶችን ፈልጎ ማግኘት እና እንዲታረም መደረጉንም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልፀዋ፡፡

አቶ ሰለሞን አክለውም የሳይበር ዓለም ተለዋዋጭ እና  -ተገማች መሆኑን በመጥቀስ ከዚህ በኃላም ከባድ የሆኑ የሳይበር  ጥቃቶች ሊደርሱ ስለሚችሉ  ሁሌም ዝግጁ ነን፤ ቴክኖሎጂዎች ላይ ስትራቴጂካል ጥናትና ምርምር ማስቀጠል እንዲሁም ከተቋማትና ባለድርሻ አካላት በጋራ በመሥራትና ዜጎቻችንን በማንቃት የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነትና ሳይበር ዲፕሎማሲያችንን በጋራ ልናስጠብቅ ይገባል ብለዋል።