የፖለቲካ ፓርቲዎች የሳይበር ደህንነትን ጉዳይ የፖሊቲካ ፕሮግራሞቻቸው አካል አድርገዉ ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 15/2014፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በሳይበር ደህንነት አጠባበቅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠና ማስከፈቻ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ ዓለም ዲጂታላይዝድ እየሆነች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃት በቁጥርም፣ በተፅዕኖም ሆነ በዓይነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት ብቻ በሀገራችን ከእጥፍ በላይ ጥቃት መጨመሩን የገለጹት ኃላፊዉ አብዛኞቹ ጥቃቶች የሚፈጸሙት ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ መሆኑንም አቶ ይድነቃቸው ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደማንኛውም ተቋም ድርጅቶቻቸውን፣ ራሳቸውን እና አባሎቻቸውን ከሳይበር ጥቃት ከመጠበቅ እንዲሁም ከቴክኖሎጂ፣ ከሰው ኃይል እና ከአሠራር ሥርዓት አኳያ ሊሠሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መድረክ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም አቶ ይድነቃቸው ገልጸዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ የሳይበር ጥቃት በሀገር ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የሳይበር ደህንነትን አንዱ አጀንዳ አድርገው በፕሮግራሞቻቸው ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በኢመደኤ የሳይበር ደህንነት ባለሙያ የሆኑት አቶ በለጠ ደስታ በሳይበር፣ በሳይበር ደህንነትና ባህሪያት፣ አሉታዊ አንድምታዎች፣ ሳይበር ለፖለቲካው ዘርፍ ያመጣው መልካም እና መጥፎ አጋጣሚ እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድረገዋል፡፡